ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ በስንዴ ምርት እየተሳተፉ ያሉ ባለድርሻ አካላትን አመሰገኑ
አዲስ አበባ፣ ጥር 22፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በስንዴ ምርት እየተሳተፉ ያሉ ባለድርሻ አካላትን አመሰገኑ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ በመልዕክታቸው ሀገራችን ስንዴን ከውጪ ለማስገባት ልታውለው የነበረውን የ1 ቢሊየን ዶላር ወጪ ለማስቀረት ተአምር የሚሠሩትን ክንደ ብርቱ አርሶ አደሮች፣ የግብርና ኤክስቴንሽን ሠራተኞች እና የግብርናውን ዘርፍ ባለድርሻ አካላት ለማመስገን እወዳለሁ ብለዋል።
ዛሬ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ፥ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ ሌሎች የመንግስት የስራ ሀላፊዎች በኦሮሚያ ክልል በመስኖ የለማ የቆላ ስንዴን ጎብኝተዋል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!