በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 10 እፎይታ የገበያ ማዕከል የደረሰው የእሳት አደጋ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለጸ
አዲስ አበባ፣ ጥር 23፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ ምሽት በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 10 እፎይታ የገበያ ማዕከል ሱቆች ላይ የደረሰው የእሳት አደጋ በቁጥጥር ስር መዋሉን የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።
ዛሬ ከምሽቱ 2:20 አካባቢ በአዲስ አበባ ከተማ አዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 10 እፎይታ የገበያ ማዕከል ሱቆች ላይ የእሳት ቃጠሎ የተነሳ ሲሆን እሳቱን ለማጥፋት እና አደጋውን ለመቆጣጠር በእሳት አደጋ መከላከያ፣ በፖሊሶች እና በአካባቢው ነዋሪዎች ርብርብ መደረጉን ገልጸዋል።
የእሳት አደጋውም በቁጥጥር ስር መዋሉን ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ሚዲያቸው አሳውቀዋል።
ጠቅላላ የተቃጠሉ የሱቆች ቁጥርና የደረሰው የጉዳት መጠንም እየተጣራ መሆኑን ገልጸዋል።
አደጋው በቁጥጥር ስር ቢውልም፤ የእሳት ቃጠሎ ዛሬ ከሰዓት በኋላ ብቻ በከተማዋ ለሁለተኛ ጊዜ የተነሳ በመሆኑ እና እሳቱ በተነሳ ጊዜ ዘረፋም ስለነበረ ጠንከር ያለ የምርምራ ስራ ተጀምሯል ነው ያሉት።
ለጋራ ሰላም ሲባል ምንም አይነት መረጃ ያለው ሰዉ ለህግ አስከባሪ እና ለፖሊስ መረጃዉን እንዲሰጥ ጠይቀዋል።
ሁሉም የከተማዋ አምራች እና ነዋሪዎች ይህን መሰል አደጋ ዳግም እንዳይከሰት ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስበዋል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!