Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ ከተማና ጉለሌ ክፍለ ከተሞች የተከሰተውን የእሳት ቃጠሎ መነሻ በማጣራት እርምጃ ይወሰዳል -ም/ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 24 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በትናንት በአዲስ ከተማና ጉለሌ ክፍለ ከተሞች የተከሰተውን የእሳት ቃጠሎ መነሻ በማጣራት እርምጃ እንደሚወሠድና በቃጠሎው ለተጎዱ ነዋሪዎች አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚደረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

ምክትል ከንቲባዋ ዛሬ ጠዋት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 እፎይታ የገበያ ማዕከል በመገኘት በእሣት ቃጠሎ የደረሰውን ጉዳት ጎብኝተው የተጎዱ ነዋሪዎችን አጽናንተዋል።

በሁለቱም አካባቢ የተነሣው እሣት ድንገተኛ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በንብረታቸው ላይ ጉዳት የደረሠባቸው ነዋሪዎች መፅናናት እንዳለባቸው ገልፀው፤ የከተማ አስተዳደሩ አስፈላጊውን ሁሉ ለማድረግ ከጎናቸው እንደሚቆም አረጋግጠዋል።

“በአደጋው የተቃጠሉ የሱቆች እና የቤቶች ብዛት፣ በጠቅላላው የደረሰው ጉዳት በፖሊስ እየተጣራ ነው” ያሉት ወይዘሮ አዳነች፤ የእሳት አደጋውን መነሻ ለማወቅ በሚደረገው ጥረት እና ለጋራ ሰላም ሲባል መረጃ ያለው ሰው ሁሉ ለህግ አስከባሪ እና ለፖሊስ መረጃውን በመስጠት እንዲተባበር ጠይቀዋል።

መሰል አደጋ ዳግም እንዳይከሰት ሁሉም የከተማዋ ነዋሪ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስበዋል።

ጉዳዩን በአፋጣኝ ለማጣራት ርብርብ እንዲደረግ ምክትል ከንቲባዋ ጥሪ ማቅረባቸውን የአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት አስታውቋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.