Fana: At a Speed of Life!

የሶማሌ ክልል መንግስት ካቢኔ አራት አጀንዳዎች ላይ ተወያየ

አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የሶማሌ ክልል መንግስት ካቢኔ አራት አጀንዳዎች ላይ ተወያይቷል።

ካቢኔው ዛሬ ባደረገው ስምንተኛ መደበኛ ስብሰባው የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሙስጠፌ ሙሃመድን ጨምሮ ሁሉም የአስፈፃሚው አካላት ተገኝተዋል ።

አጀንዳዎቹም የክልሉን መንግስት የ2013 አመተ ምህረት የስድስት ወራት የስራ አፈፃፀም መገምገም ፣ የክልሉ የስራ ዕድል ፈጠራ ኮምሽን የማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ማፅደቅ ፣ በማንኛውም ማስታወቂያዎች ቦርዶች የሶማሌኛ ቋንቋን ፅሁፎች መመሪያና ማስተካከያ እንዲሁም የክልሉ ተጨማሪ በጀት መሆናቸው ተመላክቷል።

የካቢኔ አባላቱም በቀረቡት አጀንዳዎች ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ማብራርያና ገለፃ ከተሰጠባቸው በሁዋላ ከቀረቡት አራት አጀንዳዎች መካከል የክልሉ የስራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን አዋጅ የአደረጃጀትና ሌሎች የመዋቅር ጉዳዮችና መብራራት ያለባቸው ጉዳዮች በመኖራቸው ለሌላ ጊዜ እንዲተላለፍ የወሰነ ሲሆን÷ሌሎች አጀንዳዎችን በሙሉ ድምፅ አጽድቋል።

በቀጣይ አጀንዳዎቹ ለክልሉ ምክር ቤት የሚቀርብ መሆኑን ከክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.