Fana: At a Speed of Life!

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችንና ምሩቃንን አሰልጥኖ ወደ ቴክኖሎጂው ለማስገባት የሚያስችል ሃሳብ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2012(ኤፍ.ቢ.ሲ) የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችንና ምሩቃንን በዘመናዊ የሶፍትዌር መተግበሪያ አሰልጥኖ ወደ ቴክኖሎጂ ለማስገባት ያቀደ ሃሳብ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዲኤታ ፕሮፈሰር አፈወርቅ ካሱ፥ ከሃገርኛ ድርጅት ስራ አስኪያጅ ቢያግ ሚን ጋር በቀረበው ሃሳብ ላይ ተወያይተዋል።

የቀረበው ሃሳብ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን እና ስራ ፈላጊ ምሩቃንን አስፈላጊ የኮምፒውተር ቋንቋዎችን በማሰልጠን ለማብቃት ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዲኤታ ፕሮፈሰር አፈወርቅ ካሱ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጅ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ እንደ ጃቫ ባሉ የኮምፒውተር ቋንቋ ዘርፍ በቂ የሰለጠኑ ባለሙያዎች አለመኖራቸውን ዋና ስራ አስኪያጁ ተናግረዋል።

ተማሪዎችንና ምሩቃንን በማብቃት በኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ኢንዱስትሪው ውስጥ እንዲሰሩ ለማዘጋጀት እቅድ እንዳላቸውም ነው የተናገሩት።

ፕሮፌሰር አፈወርቅ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለእቅዱ ተግባራዊነት አብሮ እንደሚሰራ ጠቅሰዋል።

ሃገርኛ በኮሪያ ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ በነበሩ ኢትዮጵያውያን የዛሬ 10 ዓመት የተሰራ አማርኛ ለመፃፍ የሚያስችል የሞባይል መተግበሪያ ስያሜ መሆኑን ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.