Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ መኮንን ከተሰናባቹ የአፍሪካ ህብረት ምክትል ኮሚሽነር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከተሰናባቹ የአፍሪካ ህብረት ምክትል ኮሚሽነር አምባሳደር ክዌሲ ኳሪቴይ ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይቱ አቶ ደመቀ ምክትል ኮሚሽነሩ በኢትዮጵያ የጋና አምባሳደር በነበሩበት ወቅት እንዲሁም በህብረቱ ምክትል ኮሚሽነርነታቸው ለሰጡት አገልግሎት ምስጋና አቅርበው በጋና እና በኢትዮጵያ መካከል ያለው መልካም ግንኙነት መጠናከር እንዳለበት ተናግረዋል፡፡
አያይዘውም በትግራይ ክልል እየተደረገ ያለውን የሰብአዊ ድጋፍ አስመልክተው ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
በህግ ማስከበር ዘመቻው ወቅት የአፍሪካ ህብረት ጉዳዩን በመረዳት ለወሰደው አቋም አድናቆታቸውን ገልጸዋል፡፡
ምክትል ኮሚሽነሩ በበኩላቸው በኢትዮጵያ በነበራቸው የቆይታ ጊዜ ስለተደረገላቸው ድጋፍ አመስግነው፤ ከኢትዮጵያውያን ጋር ያላቸውን ወዳጅነት እንደሚቀጥሉ መግለፃቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.