የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ልዑካን ቡድን በህዳሴው ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር በተመለከተ ከውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 25 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ልዑካን ቡድን በህዳሴው ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር በተመለከተ ከውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚስቴር ጋር ተወያይተዋል ፡፡
ውይይቱ የተካሄደው በውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት መሆኑ ተመላክቷል፡፡
የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፕሬዚዳንት ፌሊክስ ትሺሴኬዲኪ የአሁኑ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ናቸው ፡፡ የልኡኩ አባላት ከዶ / ር ኢ/ር ስለሺ በቀለና ከከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ወቅታዊ
ሁኔታና የሶስትዮሽ ድርድርን አስመልክቶ ተወያይተዋል ፡፡
ሚንስትሩም ኢትዮጵያ ለጋራ ተጠቃሚነትና መፍትሄ ትሰራለች በድርድሩ ረገድም ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ
አመራርን በጉጉት ትጠብቃለች ሲሉ ተናግረዋል ፡፡
ሚኒስትሩ አያይዘውም ኢትዮጵያ በሶስትዮሽ ድርድሩ ለአፍሪካ ችግሮች ለአፍሪካዊ መፍትሄዎች ለማምጣት ቁርጠኛ መሆኗን ማረጋገጣቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!