የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የ21 እጩ ዳኞችን ሹመት አፀደቀ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 25፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)ምክር ቤት 8ኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤውን አጠናቋል።
የከተማው ምክር ቤት ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ፍርድ ቤት፣በአቃቤ ህግ ቢሮና በየደረጃው ባሉ ፍርድ ቤቶች በረዳት ዳኝነት ሲያገለግሉ የቆዩ ዳኞችን ለይግባኝ ሰሚ እና መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቶች በእጩነት አቅርበዋል ።
በዚሁም ለምክር ቤቱ ቀረበው ከተሾሙት 21 ዳኞች ውስጥ 5 እጩ ዳኞችን ለአዲስ አበባ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ሲሆን 16 ቱ ዳኞችን ደግሞ ለአዲስ አበባ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት መሆኑን የከተማው ፕሬስ ሴክሬተሪ አስታውቋል።
በተጨማሪም ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለከተማው ዋና ኦዲተርነት አቶ አመንቲ መቻሉን ያቀረቡ ሲሆን ምክር ቤቱም በዝርዝር ካመረመረ በኋላ ሹመቱን አጽድቋል፡፡
ሹመቱ ከጸደቀ በኋላ ሁሉም ተሿሚዎች ቃለ መሀላ መፈጸማቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!