አቶ ደመቀ መኮንን ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሃመት ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 2፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሃመት ጋር ተወያዩ፡፡
በውይይቱ የአፍሪካ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ተፈፅሟል የተባለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ላይ ምርመራ በሚካሄድበት ሁኔታ ላይ መክረዋል፡፡
እንዲሁም የኮሚሽኑ ሊቀመንበር በዚህ ዙሪያ የኢትዮጵያ መንግስት ከህብረቱ ጋር ለመስራት ዝግጁ በመሆኑ ያላቸውን አድናቆት ገልፀዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለአፍሪካ ህብረት ሰላምና የደህንነት ምክር ቤት በትግራይ ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ ምርመራ እንዲያደርግ ጥያቄውን ማቅረባቸው የሚታወስ ነው፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!