ቤጅንግ አሸዋ በቀላቀለ ከባድ አውሎ ነፋስ ተመታች
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የቻይና ዋና ከተማ ቤጅንግ በአስርት ዓመታት ውስጥ ከፍተኛ ነው በተባለ አሸዋ በቀላቀለ አውሎ ነፋስ ተመታለች።
የቤጅንግ ሰማይ በከባድ አቧራ ተሸፍኗል ያለው የቢቢሲ ዘገባ ከተማዋ በቅርብ ጊዜያት አስተናግዳው የማታውቀው አውሎ ንፋስ መሆኑን ተገልጿል።
አውሎ ነፋሱ በከተማዋ ያልተለመደ የአየር ብክለት እንዲከሰት ማድረጉ የተገለፀ ሲሆን በአንዳንድ የከተማዋ ክፍሎች አየር ብክለት ተብሎ ከተቀመጠው ልኬት 160 እጥፍ በላይ በመሆን ብክለት ማስከተሉ ተጠቁሟል።
በመቶዎች የሚቆጠሩ በረራዎች እንዲሰረዙና አውሮፕላኖች እንዲያርፉ እንዳደረገና በሰማዩ ላይ ያልተለመደ ነገር እንዲታይ ማድረጉንም ዘገባው አመልክቷል።
ይህ አሸዋ የተቀላቀለበት ከባድ አውሎ ነፋስ በከባድ ነፋስ ምክንያት ከሞንጎሊያ የመጣ ነው ተብሏል።
በሞንጎሊያ በተለያዩ ጊዜ በተነሳ አሸዋ የቀላቀለ አውሎ ነፋስ ምክንያት የሰዎች ህይወት ማለፉና በርካቶች የገበቡበት አለመታወቁ ይነገራል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!