ጣሊያን በኢትዮጵያ ለሚካሄደው 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ የ400 ሺህ ዩሮ ድጋፍ አደረገች
አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጣሊያን መንግሥት በሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስቴር በኩል በኢትዮጵያ ለሚካሄደው 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ የ400 ሺህ ዩሮ ድጋፍ አደረገ።
ድጋፉ “የኢትዮጵያን ዴሞክራሲ ለማጠናከር ምርጫውን መደገፍ” ለተሰኘው የተመድ የልማት ፕሮግራም (ዩኤንዲፒ) ፕሮጀክት የሚውል መሆኑን ከኤምባሲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
አላማውም የምርጫ ቦርድን አቅም በማጠናከር በምርጫ ሂደቱ ግልጽና አካታች የሆነ ሂደት ለመፍጠር የሚደረገው ጥረት ማገዝ መሆኑም ተገልጿል፡፡
የድጋፍ ስምምነቱን በኢትዮጵያ የጣሊያን አምባሳደር አርቱሮ ሉዚ እና የዩኤንዲፒ የኢትዮጵያ ተወካይ ቱርሃን ሳሊህ ተፈራርመውታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!