Fana: At a Speed of Life!

የአለታ ወንዶ ምርጫ ክልል ለምርጫው የሚያገለግሉ ቁሳቁሶች የማዳረስ ስራ እየተጠናቀቀ እንደሚገኝ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የአለታ ወንዶ ምርጫ ክልል ለምርጫው የሚያገለግሉ ቁሳቁሶች የማዳረስ ስራ እየተጠናቀቀ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ከሚገኙት 119 የምርጫ ክልሎች ዉስጥ አንዱ የሆነዉ የአለታ ወንዶ ምርጫ ክልል ነገ ለሚካሄደዉ አጠቃላይ ሀገራዊ ምርጫ የሚያገለግሉ ቁሳቁሶች የማዳረስ ስራ እየተጠናቀቀ መሆኑን የክልሉ ምርጫ አስፈፃሚ አቶ እንዳለ ሙሉጌታ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ገልፀዋል ፡፡

እንደ አቶ እንዳለ ገለፃ በምርጫ ክልሉ 111የምርጫ ጣቢያዎች የሚገኙ ሲሆን፥ ከ 76ሺህ በላይ ነዋሪዎች የምርጫ ካርድ በመዉሰድ እየተጠባበቁ ይገኛሉ ብለዋል ፡፡

በአለታ ወንዶ ምርጫ ክልል ዉስጥ ለሚገኙ የገጠር ወረዳ ምርጫ ጣቢያዎች ቁሳቁስ ተከፋፍሎ መጠናቀቁን የገለፁት ምርጫ አስፈፃሚዉ ቀሪዉ በአለታ ወንዶ ከተማ ወደሚገኙት የምርጫ ጣቢያዎች የማዳረስ ስራ እያከናወኑና ይህንንም በጥቂት ሰአት ዉስጥ እንደሚጠናቀቅ አስረድተዋል ፡፡

በተያያዘ ዜና ለፋና ብሮድካስቲንግ ሃሳባቸውን የሰጡ የአለታ ወንዶ ከተማ ነዋሪዎች ምርጫ ካርድ ከመውሰድ ባለፈ ይሆነናል የምንለውን ለመምረጥ እየተጠባበቅን እንገኛለን ብለዋል፡፡

ምርጫው ሰላመዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅም ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በብስራት መንግስቱ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.