የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ20 ቢሊየን ብር በላይ አተረፈ
አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 1፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ2013 በጀት ዓመት ከ20 ቢሊዮን ብር በላይ ትርፍ ማግኘቱ ተገለጸ፡፡
የንግድ ባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ የ2013 በጀት ዓመት የስራ አፈፃጸም አስመልከተው መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
በዚህም ባንኩ በተጠናቀቀው የ2013 በጀት ዓመት ከ140 ቢሊየን ብር በላይ ተቀማጭ በማሰባሰብ አጠቃላይ ተቀማጩን 735 ቢሊየን ብር ማድረሱም ነው የተገለጸው፡፡
የውጪ ምንዛሬ ግኝት ለማሳደግ በተደረገው ጥረትም በበጀት ዓመቱ ከ2ነጥብ 86 ቢሊየን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ ተሰብስቧል፡፡
በበጀት ዓመቱ ለተለያዩ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶችና የንግድ ተቋማት 107 ቢሊየን ብር በብድርና ቦንድ ሽያጭ መልክ ያቀረበ ሲሆን፥ 60 ቢሊየን ብር ከብድር ተመላሸ ተሰብስቧልም ነው ያሉት፡፡
በባንኩ የ80 ዓመታት ታሪክ ከፍተኛ ትርፍ ማስመዝገብ መቻሉ የተጠቀሰ ሲሆን፥ አጠቃላይ ሀብቱም 999 ቢሊየን ብር መድረሱን አቶ አቤ ሳኖ አስታውቀዋል፡፡
የባንኩ ቅርንጫፎች ቁጥር ከ1ሺህ 700 በላይ ሲሆን፥ የአስቀማጭ ደንበኞች ብዛትም 31ነጥብ 4 ሚሊየን መድረሱንም ነው በመግለጫቸው ያስታወቁት፡፡
በበጀት ዓመቱ በባንኩ የዲጂታል ባንኪንግ አማካኝነት ከ529 ቢሊየን ብር በላይ ዝውውር መፈጸሙን ከባንኩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!