Fana: At a Speed of Life!

በዶሃ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለህዳሴ ግድብ የቦንድ ግዢ ፈጸሙ

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 1፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በዶሃ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን እንዲሁም የዳያስፖራ ማህበራት የ25 ሺህ የአሜሪካን ዶላር የቦንድ ግዥ ፈጽመዋል።

በቀጠር የኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ ማህበር የ15 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ዋጋ ያለው የቦንድ ግዥ በያዝነው ሳምንት ፈፅሟል።

የኢፌዲሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሳሚያ ዘካሪያ የቦንድ ግዥውን ለፈፀሙ አካላት የቦንድ ሰርተፍኬት ርክክብ ያደረጉ ሲሆን፥ ዜጎች በዚህ ወሳኝ ወቅት ለግድቡ እያሳዩት ያለው ቀጣይነት ያለው ድጋፍ የሚደነቅ መሆኑንም ተናግረዋል።

ሌሎችም ይህንኑ አርዓያነት ያለው ተግባር እንዲደግፉ አምባሳደሯ ጥሪ ማቅረባቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ኤምባሲው የቦንድ ግዥ በመፈጸም እና በሌሎች ድጋፎች የተሳተፉ ዜጎችን፣ የህዳሴ ግድብ የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ቡድን አባላት እና የዳያስፖራ አደረጃጀቶችን አመስግኗል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.