የጥፋት ሃይሎችን “በቃችሁ” በማለት ወጣቶች ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ ተጠየቀ
አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 6 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)ወጣቶች የጥፋት ሃይሎችን እኩይ ዓላማ በማክሸፍና “በቃችሁ” በማለት ለኢትዮጵያ ልማት፣ ሰላምና መረጋጋት ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ የምዕራብ እዝ ምክትል አዛዥና የመተከል ዞን ኮማንድ ፖስት አባል ብርጋዴር ጄኔራል አለማየው ወልዴ አሳሰቡ።
ከኮማንድ ፖስቱ፣ ከመተከል ዞንና ከቡለን ወረዳ የተውጣጡ አመራሮች፣ የኃይማኖት አባቶች፣ የሃገር ሽማግሌዎች እንዲሁም ወጣቶች በወቅታዊ የሰላምና ደህንነት ጉዳዮች ውይይት አካሂደዋል።
የምዕራብ እዝ ምክትል አዛዥና የመተከል ዞን ኮማንድ ፖስት አባል ብርጋዴር ጄኔራል አለማየው ወልዴ፥ ‘‘ያለፈውን ጥፋት እያነሱ ነገሮችን ከማባባስ ይልቅ ሰላም የሚመጣው በሰላማዊ መንገድ ብቻ መሆኑን በመረዳት ለቀጣይ አብሮነትና አስተማማኝ ሰላም መስራት ይገባል’’ ብለዋል።
በመተከል ዞን ተፈጥሮ የነበረውን ግጭት በዘላቂነት ለመፍታት የመንግስትን የሰላም ጥሪ የተቀበሉ ታጣቂዎች በሁለት ዙር የተሃድሶ ስልጠና በመውሰድ ከማህበረሰቡ ጋር ተቀላቅለው ሰላማዊ ኑሯቸውን እንዲመሩ እየተደረገ መሆኑን መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!