Fana: At a Speed of Life!

ከሳዑዲ ዓረቢያ 2 ሺህ 42 ዜጎች ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 7 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከሳዑዲ ዓረቢያ 2 ሺህ 42 ዜጎች ወደ ሀገራቸው ተመለሱ።
በሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ ዜጎቻችንን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ በተያዘው እቅድ መሰረት በርካታ ዜጎቻችን በየቀኑ ወደ አገራቸው እየተመለሱ ይገኛሉ።
በዚህ መሰረትም በትናንትናው ዕለት 229 ሴቶችንና 136 ህጻናትን ጨምሮ በአጠቃላይ 2 ሺህ 42 ዜጎቻችን ወደ ሀገራቸው ገብተዋል።
ተመላሾቹ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላትን ያቀፈው ኮሚቴ ተገቢው አቀባበል አድርጎላቸዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.