የሲቪክ ማህበራት በምርጫው ያሳዩትን አቅም በሌሎች ሀገራዊ አጀንዳዎች ሊጠቀሙበት ይገባል -ምሁራን
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 7፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ሃገር በቀል የሲቪክ ማህበራት በምርጫው ያሳዩትን አቅም በሌሎች ሀገራዊ አጀንዳዎች ሊጠቀሙበት እንደሚገባ ምሁራን ገለፁ፡፡
በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስና ዓለም ዓቀፍ ግንኙነት ተመራማሪው ሱራፌል ጌታሁን ÷ቀደም ሲል በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱ ሲቪክ ድርጅቶችና ማህበራትን አስመልክቶ የወጣው ህግ ማህበራቱን አስሮ የቆየ መሆኑን ይናገራሉ፡፡
በአንጻሩ አሁን ላይ የህግ መሻሻል በመኖሩ ማህበራቱ በምርጫው ወቅት የተሻለ ሥራ እንዲሰሩ አስችሏቸዋል ነው ያሉት፡፡
የሀገር በቀል ሲቪክ ማህበራትን አቅም ማደርጀት ከአንድ ሰሞን የምርጫ እና መሰል ስራ ያለፈ ጠቀሜታ እንዳለው የሚናገሩት ደግሞ በዲላ ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ቤት መምህሩ ሄኖክ አሻግሬ ናቸው፡፡
ማህበራቱ ህዝቦችን ማቀራረብና ብሔራዊ መግባባት ላይ በትኩረት መስራት እንዳለባቸውም ነው ያሳሰቡት፡፡
የሲቪክ ማህበራት ቀጣይ ትኩረት ሀገር በአንድነቷ የምትቀጥልበትን እንዲሁም ሰላምና ደህንነት የሚሰፍንበትን መንገድ ማበጀት ላይ መሆን እንዳለበት ምሁራኑ ተናግረዋል፡፡
ማህበራቱን የማጠናከር እና የመደገፍ ስራ ከህብረተሰቡ እንደሚጠበቅም ነው ምሁራን ያሳሰቡት፡፡
በአፈወርቅ እያዩ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!