መከላከያ ሰራዊትና የፌደራል ፖሊስ የቀጠናውን ሰላም እና የዜጎችን ደህንነት ለመጠበቅ በአስተማማኝ ቁመና ላይ ይገኛል – ብርጋዴር ጄኔራል አለማየሁ ወልዴ
አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 8 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሃገር መከላከያ ሰራዊትና የፌደራል ፖሊስ የቀጠናውን ሰላም እና የዜጎችን ደህንነት ለመጠበቅ በአስተማማኝ ቁመና ላይ እንደሚገኝ የምዕራብ ዕዝ ምክትል አዛዥ እና የመተከል ዞን የተቀናጀ ግብረኃይል ኮማንድ ፖስት አባል ብርጋዴር ጄኔራል አለማየሁ ወልዴ ገለጹ።
እንደ ጄኔራል አለማየሁ ገለፃ፥ ኮማንድ ፖስቱ ባከናወናቸው ተግባራት በመተከል ዞን የተለያዩ አካባቢዎች ከቀያቸው ተፈናቅለው የነበሩ ከ52 ሺህ በላይ ዜጎችን በየወረዳቸው በመመለስ የተመረጡ ማዕከላት እንዲያርፉ ተደርጓል፡፡
የአገር መከላከያ ሰራዊትና የፌደራል ፖሊስ አባላትም በየማዕከላቱ እንዲያርፉ የተደረጉ ዜጎችን ሰላምና ደህንነት ሃያ አራት ሰዓት ለመጠበቅ ዝግጁ መሆናቸውም ነው የተገለፀው፡፡
ኮማንድ ፖስቱ በየወረዳ መጠለያ ማዕከላት እንዲያርፉ የተደረጉ ዜጎችን ወደ የቀበሌዎቻቸው ሄደው አምራች የሚሆኑበትን መንገድ ለማመቻቸት የእርቀ ሰላምና ሌሎች ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!