Fana: At a Speed of Life!

ኳታር የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ የቅድመ ኢንቨስትመንት ውይይት አካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 8 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ዶሃ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በኳታር ትልቁ የወተት አምራችኢንዱስትሪ ጋር የቅድመ ኢንቨስትመንት ውይይት በበይነ መረብ አኳሂዷል።
በትናንትናው ዕለት ኤምባሲው ባዘጋጀው የበይነ መረብ የቅድመ ኢንቨስትመንት ውይይት ላይ÷ በኢትዮጵያ የሚመለከታቸው የመንግስት ተቋማት በኳታር በወተትና የወተት ምርት አምራች ታዋቂ ከሆነው ባላድኒ የምግብ ኢንዱስትሪ ጋር ተወያይተዋል።
የዚህ ውይይት ዓላማም በኢትዮጵያ ያለው መጠነ ሰፊ የኢንቨስትመንት አማራጮችን ለማስተዋወቅ ያለመ መሆኑ ተመላክቷል።
በዚህ ውይይት ላይ በኢትዮጵያ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች እና ባለሙያዎች ከግብርና ሚኒስቴር፣ የኢንቨስትመንት ኮሚሽንን ጨምሮ ዘርፉ ከሚመለከታቸው ተቋማት መሳተፋቸው ተገልጿል።
በስብሰባውም ላይ ተሳታፊ የሆኑት ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች እና ባለሙያዎች በዘርፉ በኢትዮጵያ ስላለው መጠነ ሰፊ የኢንቨስትመንት አማራጮች ገለጻ አድርገዋል።
በተጨማሪም ለባለሃብቶች በኢትዮጵያ ስላለው ማበረታቻ ፣ የመሰረተ ልማት አቅርቦት እንዲሁም በዘርፉ ስላለው ትልቅ የገበያ ዕድል የመንግሥትን ድጋፍ አብራርተዋል ፡፡
የኳታሩ የባላድኒ የምግብ አምራች ኢንዱስትሪ ሃላፊዎች በበኩላቸው÷ በበዘርፉ ያላቸውን የካበተ ልምድ አጋርተዋል።
በተጨማሪም በኢትዮጵያ በኢንቨስትመንት ዘርፍ ለመሰማራት ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላቸው እና ከመንግስት ጋር በጋራ ለመስራት ያላቸውን ፍላጎት መግለጻቸውን ኳታር ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People Reached
85
Engagements
Boost Post
83
2 Shares
Like

 

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.