Fana: At a Speed of Life!

ፍትህ በማግኘት ሂደት ውስጥ  ባህላዊ ፍርድ ቤት  ጉልህ ድርሻ አለው – አቶ ሽመልስ አብዲሳ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ፍትህ  በማግኘት  ሂደት ውስጥ ባህላዊ ፍርድ ቤት ጉልህ ድርሻ  እንዳለው የኦሮሚያ  ክልላዊ መንግስት  ርዕሰ መስተዳድር  አቶ ሽመልስ አብዲሳ  ተናገሩ፡፡

በክልላችን ህዝብ እውቀት እና ፍልስፍና ላይ በመመስረት ከውጭ ሀገራት የምንቀዳቸውን ነገሮች በመጨመር የተሻለ ሁኔታን መፍጠር ተገቢ ነው  ብለዋል፡፡

ጨፌ ኦሮሚያ የኦሮሚያ ባህላዊ ፍርድ ቤትን ለማቋቋም የተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ ላይ በጥልቀት ከተወያየ በኋላ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።

ይህ ረቂቅ አዋጅ መፅደቁ  ጨፌው ከወሰናቸው ሁሉ ታሪካዊው ውሳኔ ነው  ሲሉም ርዕሰ መስተዳድሩ ገልጸዋል።

ባህላዊ ፍርድ ቤቱ የሃሰት ምስክር እና የሃሰት ክስን  በማስቀረት ረገድ  ጉልህ ሚና እንደሚኖረውም አቶ ሽመልስ መናገራቸውን ከኦቢኤን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.