Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የልዑካን ቡድን ከአምባሳደር መለስ ዓለም ጋር ተወያየ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 11፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የልዑካን ቡድን በኬንያ ከኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር መለስ ዓለምና በኬንያ ከሚገኙ የተለያየ የሃይማኖት ተቋማት የሃይማኖት አባቶች ጋር ተወያየ፡፡
በውይይቱም ከሀገር ውጭ ሁለተኛ የሆነውን የጉባኤውን ቅርንጫፍ በኬንያ ማደራጀት ስለሚቻልበት ሁኔታ ላይ ምክክር የተደረገ ሲሆን ÷ከሁሉም እምነት ተቋማት የተውጣጡ የአደራጅ ኮሚቴም ተሰይመዋል ።
በዚህ ወቅት አምባሳደር መለስ የልዑካን ቡድኑ ወደ ናይሮቢ መምጣት ኢትዮጵያውያንን ለማደራጀት እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ አመስግነው ከዚህም በኋላ የኤምባሲው ሙሉ ድጋፍ እንደማይለየው አረጋግጠዋል ።
የጉባኤው ቅርንጫፍ መደራጀቱ በኬንያ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ከእምነት ጋር በተያያዘ የሚኖራቸው መብቶች እና ጥቅሞች ለማስጠበቅ የሚረዳ ከመሆኑም በላይ ኢትዮጵያዊያንን ለሀገራቸው ጉዳይ ተሳታፊ እንደሚያደርጋቸው ገልጸዋል ።
ከዚህም ባለፈ የኢትዮጵያ እና ኬንያ ወዳጅነት፣ትብብርና አጋርነትን እንደሚያጠናክር ተናግረዋል ።
በመጨረሻም የጉባኤው ጠቅላይ ፀሐፊ ኢትዮጵያዊያን ከመቼውም ጊዜ በበለጠ የውስጥ አንድነታቸውን በማጠናከር ለሀገራዊ አንድነት ተባብረው እንዲሰሩ ለኮሚኒቲውና ለሃይማኖት አባቶች ጥሪ ማቅረባቸውን ከየኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.