የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የአረፋ በዓልን ምክንያት በማድረግ የህጻናት ማሳደጊያ ማዕከላትን ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 11፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ የአረፋ በዓልን ምክንያት በማድረግ የህጻናት ማሳደጊያ ማዕከላትን ጎብኝተዋል::
ርዕሰ መስተዳድሩ ከክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በጋራ በመሆን ነው የአረፋ በዓልን ምክንያት በማድረግ ተስፋና ሰዓዳ የህጻናት ማሳደጊያ ማዕከላትን የጎበኙት፡፡
በዚህ ወቅትም የህፃናት ማሳደጊያዎቹ እያከናወኑት ያለውን አበረታች ተግባራት አጠናክረው መቀጠል እንደሚገባ የገለፁት አቶ ኦርዲን÷ ማዕከላቱ በዋነኝኝነት በህብረተሰቡ የሚደገፉበት አሰራር መዘርጋት እና ለተግባራዊነቱም መረባረብ አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡
የክልሉ መንግስትም ለህፃናቱ ማሳደጊያ ማዕከላት የሚያደርገውን ድጋፍ እንደሚያጠናክር ጠቁመው÷ የአረፋ በአልን በማስመልከት ለህፃናት ማሳደጊያ ማዕከላቱ የሥጦታ እና የገንዘብ ድጋፍ ማድረጋቸውን ከሀረሪ ክልል የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!