Fana: At a Speed of Life!

የመሰዋትና የአንድነት በዓል በመሆኑ የፈጣሪን ትዕዛዝ ማክበር ይገባል-ሃጂ ሱልጣን አማን

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 13፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አረፋ የመሰዋት እና የአንድነት በዓል በመሆኑ የፈጣሪን ትዕዛዝ ማክበር ከምእመናን እንደሚጠበቅ የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሃጂ ሱልጣን አማን ተናግረዋል፡፡
1ሺህ 442ኛው የኢድ አል አደሃ (አረፋ) በዓል በአዲስ አበባ ስቴዲየም በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስነ ስርዓቶች እየተከበረ ነው፡፡
በበዓሉ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ዑመር እድሪስን ጨምሮ ሌሎች በርካታ የእምነቱ አባቶች ተገኝተዋል።
የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሃጂ ሱልጣን አማን አረፋ የመሰዋት እና የአንድነት በዓል በመሆኑ የፈጣሪን ትዕዛዝ ማክበር ከምእመናን ይጠበቃል ብለዋል፡፡
ከክፋት ይልቅ ለቀናነት፣ ከመጥበብ ይልቅ ለመስፋት መትጋት እንደሚያስፈልግም ነው ያሳሰቡት፡፡
እስልምና የሰላም ሃይማኖት ነው ያሉት ፕሬዝዳንት ሃጂ ሱልጣን÷ ሁሉንም የውስጥ ችግሮች በሰላም መፍታት እንደሚገባም አንስተዋል፡፡
ሀገራችን ከፍ ለማድርግ በተለያዩ የልማት ስራዎች ላይ በአንድነት እና በርብርብ በመስራት ከድህነት መላቀቅ እንደሚገባም ጥሪ አቅረበዋል፡፡
የእምነቱ ተከታዮች በአሉን ሲያከብሩ የእምነቱ አስተምህሮ በሚያዘው ልክ ያለው ለሌለው አካፍሎ፣ የተፈናቀሉትን አስቦና የተቸገሩትን በመርዳት መሆን እንዳለበት አሳስበዋል፡፡
ለእምነቱ ተከታዮች እንኳን 1ሺህ 442ኛው የኢድ አል አደሃ (አረፋ) በዓል አደረሳችሁ ብለዋል።

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.