Fana: At a Speed of Life!

የህዳሴው ግድብ ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌት ለቀጠናው እድገትና ትብብር መለያ ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የህዳሴው ግድብ ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌት በአካባቢው ችግር ካለመፍጠሩ ባሻገር ለቀጠናው እድገትና ትብብር መለያ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለፁ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትዊተር ገፃቸው በአረብኛ ቋንቋ ባስተላለፉት መልዕክት የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌት በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት መከናወኑን ገልፀዋል፡፡
ይህም በታችኛው ተፋሰስ ሃገራት ላይ ችግር እንደማይፈጥር ጠቁመው ስጋት እንዳይኖርም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው የህዳሴው ግድብ እውነተኛ ሀብት ሆኖ የጋራ ዕድገትና ትብብር መለያ ሆኖ ይቀጥላል ብለዋል ፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.