ከአዲስ አበባ ወደ ጎጃም የሚወስደው መንገድ በናዳ ምክንያት ተዘጋ
አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 7፣2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከአዲስ አበባ ወደ ጎጃም በሚወስደው መንገድ ዓባይ በረሃ በመባል በሚታወቀው አካባቢ ባጋጠመ የድንጋይ መንሸራተት ናዳ የትራንስፖርት አገልግሎት መስተጓጎሉ ተገለፀ፡፡
የድንጋይ መንሸራተት ናዳው የደረሰው በዓባይ በረሃ አከባቢ ልዩ ስሙ ፍልቅልቅ በሚባለው ስፍራ ዛሬ ሌሊት መሆኑ ታውቋል፡፡
ችግሩን በፍጥነት ለመቅረፍም አሰቸኳይ ጥገና የሚያደርግ ግብረ ሃይል በመላክ በስፍራው ከሚገኘው አሰቸኳይ የጥገና ቡድን ጋር እየተሰራ መሆኑን ከኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡