በበጀት አመቱ ለሕዳሴ ግድብ 2 ቢሊየን 49 ሚሊየን ብር ድጋፍ ተደረገ
አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 19 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በተያዘው ዓመት ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ከህብረተሰቡ 2 ቢሊየን 49 ሚሊየን ብር መሰብሰቡን የግድቡ ግንባታ ሕዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት ገለጸ።
ጽህፈት ቤቱ ዛሬ በሰጠው መግለጫ እንዳስታወቀው÷ በተያዘው ዓመት ከህብረተሰቡ የተሰበሰበው ገንዘብ የግድቡ ግንባታ ከተጀመረ እስካሁን ከተደረገው ድጋፍ ከፍተኛው ነው።
የጽህፈት ቤቱ የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ኃይሉ አርዓያ እንደገለጹት÷ በቀደሙት ጊዜያት በዓመት ይሰበሰብ የነበረው ከፍተኛው ገንዘብ ከ1 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር በልጦ አያውቅም፡፡
በተያዘው ዓመት በህብረተሰቡ ዘንድ የታየው ከፍተኛ ተሳትፎ ለገቢው መጨመር ምክንያት መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
“ግድቡ የእኔ ነው” በሚል በሞባይል አጭር የፅሁፍ መልዕክት 8100 A በተደረገ አስተዋጽኦ 132 ሚሊየን ብር የተገኘ ሲሆን ከዳያስፖራው ተሳትፎ ደግሞ 134 ሚሊየን ብር እንደተገኘ ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!