Fana: At a Speed of Life!

ከዳያስፖራው ማህበረሰብ አባላት ለህዳሴ ግድብ ከ1 ነጥብ 1 ሚሊየን ዶላር በላይ ተሰበሰበ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 19 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በውጭ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለታላቁ ህዳሴ ግድብ 1 ነጥብ 1 ሚሊየን ዶላር በላይ ተሰበሰበ፡፡

በአሜሪካ  የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከበድር ኢትዮጵያ እና ኡስታዝ ጀማል በሽር ጋር በመሆን በ’ጎ ፈንድሚ’ ሲያካሂድ የቆየው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም የማጠናቀቂያና የምስጋና መርሃ ግብር ዛሬ ተሂዷል፡፡

በመድረኩ  በ’ጎ ፈንድሚ’ ሁለት ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ከዳያስፖራው አባላት ለህዳሴ ግድብ 1ሚሊየን 110 ሺህ የአሜሪካ  ዶላር መሰብሰብ መቻሉን  በአሜሪካ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ፍጹም አረጋ  ተናግረዋል፡፡

አምባሳደር  ፍጹም  ጉዳዩን አስመልክተው በትዊተር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ ÷የገንዘብ ማሰባሰቢያ ፕሮግራሙን ላስተባበሩ እና ድጋፍ ላደረጉ የዳያስፖራ አባላት ምስጋና አቅርበዋል፡፡

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.