በኮንታ ልዩ ወረዳ የሚገኙ የፀጥታ አካላት ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ያላቸውን ድጋፍ ገለጹ
አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 20 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኮንታ ልዩ ወረዳ የሚገኙ የፀጥታ አካላት ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ያላቸውን ድጋፍ በሰልፍና ፖሊሳዊ ትርዒት ገለጹ።
በሰልፉ ተመላሽ መከላከያ ሰራዊት አባላት፣ የልዩ ሀይል ፖሊስ፣ ማረሚያ ተቋምና ሚሊሻ አባላት ተሳታፊ የነበሩ ሲሆን የአካባቢው ነዋሪዎች ታድመዋል።
የልዩ ወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ፋንታሁን ብላቴ፥ ሀገራችን ኢትዮጵያ ለዘላለም ክብሯንና ነጻነቷን አስከብራ የኖረች ፣ የጥንት ስልጣኔ ባለቤት የሆነች በህዝቦቿ አንድነት ዓለም አቀፋዊ ጫናችንዎችን ተቋቁማ ነጻነቷን ያስከበረች ገናና ሀገር መሆኗን ገልፀዋል።
የኢትዮጵያ ቁርጥ ቀን ልጆች የጥንት አባቶች ጠብቀው በክብር ያቆዩዋትን ኢትዮጵያ ዛሬም ያን ገናናነቷን በተባበረ ክንዳቸው ለማስቀጠል ከጎናቸው ልንቆም ይገባልም ነው ያሉት።
የልዩ ወረዳው የጸጥታው መዋቅር አመራርና አባላት በዛሬው ቀን ለእናት ሀገር አለኝታነታቸውን ለማረጋገጥና ጁንታውን በመቃወም ላሳዩት ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበው ጦሪነቱ በድል እስከሚጠናቀቅ ድረስ ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል።
በሰልፉም በርካታ መፈክሮችና ሀገራዊ አንድነትን የሚያሳዩ ትዕንቶች የታዩ ሲሆን፥ የጸጥታው መዋቅሮች የኢትዮጵያን የብልጽግና ጉዞ በጋራ ለማስቀጠል ዛሬም ነገም ሁልጊዜም ኢትዮጵያን ለማዳን በጋራ እንደሚዘምቱ ማስታወቃቸውን ከኮንታ ልዩ ወረዳ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!