Fana: At a Speed of Life!

አቶ ሽመልስ አብዲሳ በ650 ሔክታር መሬት ላይ በክላስተር የለማ ማሳን ጎበኙ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ የተመራው ልዑክ ቡድን በአዳሚ ቱሉ ጂዶ ኮምቦልቻ ወረዳ በ650 ሔክታር መሬት ላይ በክላስተር የለማ የስንዴ፣ ቦቆሎ እና ቦሎቄ ሰብልን ጎብኝቷል፡፡

በዘንድሮው ምርት ዘመን እንደ ኦሮሚያ በመስኖ ለማልማት ከታቀደው 6 ነጥብ 3 ሚሊየን ሄክታር መሬት ውስጥ እስካሁን 6 ነጥብ 1 ሚሊየን ሄክታሩ በሰብል መሸፈኑን ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ለማዳከም አሸባሪዎቹ ህወሓት እና ሸኔ እያካሔዱት ያለውን የሽብር ተግባር ህብረተሰቡ ከመመከት ጎን ለጎን የልማት ስራውን በመከወን ምርታማነቱን ለማሳደግ በጥምረት መስራት ይጠበቅበታል ሲሉ አሳስበዋል፡፡

መንግስት የሀገሪቱን ሉአላዊነት ለማስከበር አሻባሪዎቹን በመደምሰስ የልማት ስራውን ለማስቀጠል በቁርጠኝነት ይሰራልም ነው ያሉት፡፡

በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪ ዶክተር ግርማ አመንቴ በበኩላቸው÷ በዘንድሮው የምርት ዘመን ለማልማት ከታቀደው 6 ነጥብ3 ሚሊየን ሄክታር መሬት እስካሁን 3 ነጥብ 4 ሚሊየን ሄክታር መሬት በክላስተር መልማቱን ገልጸዋል፡፡

ማሳቸው የተጎበኘ አርሶ አደሮችም የግብርና ባለሙያ የሚሰጣቸውን ሙያዊ ምክር ተግባራዊ በማድረግ ካለሙት ሰብል ከፍተኛ ውጤት እንደሚጠብቁ መግለጻቸውን ኦቢኤን ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.