ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲዎች የአስተዳደር ቢዝነስ ልማትና የአይሲቲ ፎረም ከነገ ጀምሮ ይካሄዳል
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 26፣ 2013 (ኤፍ ቢሲ) ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲዎች የአስተዳደር ቢዝነስ ልማትና የአይሲቲ ፎረም በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት ከነገ ጀምሮ ይካሄዳል፡፡
ከ40 የሚበልጡ ዩኒቨርሲቲዎች በሚሳተፉበት በዚህ ፎረም ላይ በዲጂታል መሠረተ ልማት፣ በመረጃ ደህንነትና በቴክኖሎጂ አጠቃቀም ዙሪያ ውይይት ይደረጋል ተብሏል።
የድሬደዋ ዩኒቨርስቲ የመረጃና መገናኛ ቴክኖሎጂ ዳይክተሩ አቶ ስንትአየሁ ዓለሙ እንደገለፁት÷ በፎረሙ መንግስት ወደ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ለመሸጋገር የያዘውን ዕቅድ ለማሳካት የሚያግዙ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት ይደረግላቸዋል ብለዋል።
ከዚህም በተጨማሪ ዩኒቨርስቲው በ195 ሚሊየን ብር ያስገነባቸው የዳታ ማዕከልና የጊቢ ኢንተርኔት ማስፋፊያ ስራዎች ይመረቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በእዮናዳብ አንዱዓለም
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!