Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪው ቡድን በእምነት ተቋማት ላይ እያደረሰ ያለው ዉድመት በአለም ህዝብ ሊወገዝ ይገባል-የሀይማኖት  አባቶች

 

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው የህወሓት ቡድን በእምነት ተቋማት ላይ ያደረሰውን ውድመት የአማራ ክልል የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ አውግዟል።

ጉባኤዉ አሸባሪዉ ቡድን በጨጨሆ መድሃኒያለም ካቴድራል ገዳም ያደረሰዉን ጉዳት ዛሬ ጎብኝቷል።

ገዳሙን ጨምሮ በደቡብ ጎንደር ዞን 7 አብያተ ክርስቲያናት ላይ ከፍተኛ ውድመት መፈፀሙን የዞኑ ሀገረስብከት ዋና ስራ አስኪያጅ ሊቀ ስዩማን ቀሲስ ምህረት ሞላ ተናግረዋል።

የባህርዳር ሀገረ ስብከት የካህናት አገልግሎት ክፍል ሀላፊ መላከ ምህረት መምህር ፈለገ ጥበብ፥ ቡድኑ የፈፀመዉ ድርጊት በአለም የጦርነት ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ አሳፋሪ እና አስነዋሪ ድርጊት ነው ብለዋል።

የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ምክርቤት ፕሬዝዳንትና የጉባኤው ምክትል ሰብሳቢ ሼህ ሰይድ ሙሀመድ በበኩላቸው፥ አሸባሪው በገዳሙና በሌሎች አብያተ ክርስቲያናት ላይ የሰነዘረው ጥቃት በሀገር ላይ የደረሰ ጥፋት መሆኑን ተናግረዋል።

ጉዳት የደረሰባቸውን የእምነት ተቋማት መገንባት ወደ ቀደመው አገልግሎታቸው እንዲመለሱ ማድረግ ላይ የየትኛውም እምነት ተከታዮች በጋራ መሳተፍ እንደሚገባቸው የሀይማኖት አባቶቹ ጥሪ አቅርበዋል።

በዙፋን ካሳሁን እና ምንይችል አዘዘው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.