ህወሓት በአፋር 4 ወረዳዎች በፈጸመው ወረራ በርካታ ውድመት አድርሷል
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሽብር ቡድኑ ህወሓት በአፋር አራት ወረዳዎች በፈጸመው ወረራ በርካታ ውድመት አስከትሏል፡፡
ቡድኑ በወረራ ይዞ በቆየባቸው አካባቢዎች ዘረፋ ከመፈጸ ባለፈ በርካታ የመንግስት መስሪያ ቤቶች አና የግለሰብ ንብረቶች ላይ ውድመት አድርሷል፡፡
አሁን ላይ አሸባሪው ቡድን ከአፋር ምድር ሙሉ ለሙሉ ተጠራርጎ የወጣ ሲሆን÷ባደረሰው ዘረፋና ውድመት ግን የአከባቢው ነዋሪዎች ተመልሰው ለመኖር ከባድ ሆኖባቸዋል፡፡
ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በእዋ፣አውራና ያሎ ወረዳዎች ተገኝቶ ባደረገው ምልከታም የነዋሪዎች እንቅስቃሴ አነስተኛ መሆኑን ለመታዘብ ችሏል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!