Fana: At a Speed of Life!

የኢሬቻ ፌስቲቫል እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) የኢሬቻ ፌስቲቫል በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡

በመርሃ ግብሩየአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ÷ኢሬቻ የፍቅርና የሰላም በዓል ነው፤ ወንድማማችነትን በማጠናከርም ቁልፍ ሚና አለው ብለዋል።

በአዲስ አበባ የሚከበረው የሆራ ፊንፊኔ በዓል ዳግም መከበር ከጀመረ ሦስተኛ አመቱን መያዙን የተናገሩት ከንቲ ባዋ ለከተማዋ ተጨማሪ የቱሪዝም መልክ መሆኑን አንስተዋል።

ኢሬቻ የምስጋና በዓል ነው ያሉት ወይዘሮ አዳነች ህይወታቸውን በመስጠት ሀገር ያቆሙ ጀግኖችን እናመሰግናለን ብለዋል።

እንዲሁም ኢሬቻ ክረምቱ በበጋ መለወጥ ብቻ ሳይሆን ወደ ተስፋ መሻገርን ያሳያል ያሉም ሲሆን ÷ ዘንድሮ አዲስ መንግስት ምስረታና በፈተናዎች ውስጥ መከበሩ ደግሞ ልዩ እንደሚያደርገው ተናግረዋል።

በአፈወርቅ እያዩ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.