Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ የአዕምሮ ጤና ተጠቂዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 30፥ 2014 ዓ.ም( ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የአዕምሮ ጤና ተጠቂዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ እንደሚገኝ በጤና ሚኒስቴር የፕሮግራም ሚኒስትር ዴኤታ ጽህፈት ቤት ሃላፊና አማካሪው አቶ ፍቃዱ ያደታ አስታውቀዋል።

በኢትዮጵያ የአዕምሮ ጤና ቀን በድሬደዋ ከተማ አዘጋጅነት “የአዕምሮ ጤናን ለሁሉም እውን እናድርግ” በሚል መሪ ቃል እየታሰበ ሲሆን፥ የሚታሰበውም በዓለም ለ30ኛ፥ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ10ኛ ጊዜ ነው።

በዚሁ ጊዜ ኢትዮጵያ የአዕምሮ ጤና ተጠቂዎች ቁጥር እየጨመረ እንደሚገኝ በጤና ሚኒስቴር የፕሮግራም ሚኒስትር ዴኤታ ጽህፈት ቤት ሃላፊና አማካሪው አቶ ፍቃዱ ያደታ አስታውቀዋል።

ሚኒስተር መስሪያ ቤቱ የህመሙን ተጠቂዎች ቁጥር ለመቀነስ ለቀጣዮቹ አምስት ዓመታት የሚያገለግል ስትራቴጂያዊ ዕቅድ በማዘጋጀት እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ነገር ግን በዘርፉ በቂ የሰለጠነ ባለሙያ አለመኖርን ጨምሮ የአመለካከት ክፍተቶችና ምጣኔ ሀብታዊ ጉዳዮች ስትራቴጂካዊ ዕቅዱ ተግባራዊ እንዳይሆን ተግዳሮት መሆኑን ገልፀዋል።

በአሁኑ ወቅት በዓለም የአዕምሮ ጤና ህመም ተጠቂዎች ቁጥር 1 ቢሊየን የተሻገረ ሲሆን፤ በየዓመቱ 3 ሚሊየን ሰዎች ከህመሙ ጋር ተያይዞ ለሞት ይጋለጣሉ።

የጤና ሚኒስቴር የአዕምሮ ጤና ክብካቤ ስትራቴጂካዊ ዕቅዱ ተግባራዊ እንዲሆን ይሰራል ያሉት ደግሞ በሚኒስቴሩ የበሽታ መከላከልና መቆጣጠር ዳይሌክቶሬት ዳይሌክተር ወይዘሮ ህይወት ሠለሞን ናቸው።

ያለ አእምሮ ጤና የትኛውም ጤና ሊታሰብ አይችልም ያሉት ዳይሌክተሯ፥ የአእምሮ ጤናን አገልግሎትን ከሌሎች የጤና ዘርፎች ጋር በማቀናጀት የአምስት አመቱ መሪ ፕላን እውን እንዲሆን ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።

በተመሳሳይ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ሃላፊ ወይዘሮ ለምለም እንዳሉት፥ በድሬዳዋ ከተማ ከሚስተዋሉት ለህመሙ አጋላጭ ሁኔታዎች አንፃር የህሙሙ ተጠቂዎች ቁጥር እየጨመረ ይገኛል።
ባሳለፍነው ዓመት ብቻ ለ8 ሺህ 200 ህመምተኞች አስተዳደሩ ህክምና እንዲሰጣቸው መደደረጉንም ጠቅሰዋል።

ይህንኑ የህመሙን ተጋላጭነት ለመቀነስም መገናኛ ብዙሃንን ጨምሮ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ ነው ብለዋል።

በእዮናዳብ አንዱዓለም

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.