የጎንደር ከተማ ምክር ቤት አቶ ዘውዱ ማለደን ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አድርጎ ሾመ
አዲስ አበባ፣ጥቅምት 3፣2014 (ኤፍ ቢሲ) ምክር ቤቱ 4ኛ ዙር 9ኛ አመት1ኛ አስቸኳይ ጉባኤውን እያካሄደ ይገኛል።
በጉባኤው አቶ ዘውዱ ማለደ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ሆነው ከተማዋን እንዲመሩ በሙሉ ድምፅ ተመርጠው ተሹመዋል።
በተጨማሪም ጉባኤው አቶ ባዩ አቡሃይ ክብረት ምክትል ከንቲባ አድርጎ ሰይሟል።
በተያያዘም የጎንደር ከተማ ብልጽግና ፓርቲ የኃላፊዎች ሹመት ተሰጥቷል።
በዚህም አቶ አወቀ አስፈሬ ሁነኛውን የጎንደር ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ኃላፊ ፤ ወ/ሮ ደብሬ የኃላ ደመቀን የጎንደር ከተማ ብልጽግና ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ እንዲሁም አቶ አዝመራው ተዘራ በላይ የጎንደር ከተማ ብልጽግና አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል።
በሙሉጌታ ደሴ
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!