በኡጋንዳ የሚኖሩ የሱማሌ ክልል ተወላጆች በአገራቸው በንግድና ኢንቨስትመንት ለመሰማራት ዝግጁ መሆናቸውን ገለጹ
አዲስ አበባ፣ጥቅምት 3፣2014 (ኤፍ ቢሲ) በኡጋንዳ የኢትዮጵያ አምባሳደር ዓለምፀሐይ መሠረት በኡጋንዳ በንግድና ኢንቨስትመንት ተሰማርተው ከሚኖሩ የሱማሌ ክልል ተወላጆች ጋር የአገራቸውን ምርቶች በኡጋንዳና በአጎራባች አገራት ለማከፋፈል እንዲሁም በኢንቨስትመንት ላይ ለመሰማራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል።
በውይይቱ በኡጋንዳ በተለያዩ የንግድ እና ኢንቨስትመንት መስክ የተሰማሩ ባለሃብቶች የተገኙ ሲሆን፥ ተሳታፊዎቹም በኡጋንዳና በቀጠናዊ ገበያ ያካበቱትን የንግድ ተሞክሮ ተጠቅመው የኢትዮጵያን ምርቶች በነዚህ ሰፊ ገበያ የማቅረብ ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላቸው አስረድተዋል።
ተሳታፊዎቹ በአሁን ወቅት አገራቸው በተለያዩ ተፅኖ ውስጥ ባለችበት ወቅት የድርሻቸውን ለማበርከት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።
በተለይም በኡጋንዳ ያለውን ነጻ የንግድ ዞን /Free trade zone/ በመጠቀም ወደ ሌሎች አጎራባች አገራት ገበያ በቀላሉ መድረስ መቻሉን በማስታወስ ፥የኢትዮጵያ ምርት የሆኑትን ለምሳሌ አትክልትና ፍራፍሬ፣ የቆዳ ውጤቶች፣ ጨርቃጨርቅ እና ሌሎች የፋብሪካ ውጤቶችን በሰፊው ወደ ቀጠናው ለማቅረብ አቅም እንዳላቸውና ንግዱን ለማሳለጥ እንቅፋት የሚሆኑ፣ ከመረጃ ክፍተት እንዲሁም ከታሪፍ ጋር በተያያዘ ያሉ ችግሮች በቅድሚያ መፈተሽ እንዳለባቸውም ገልፃዋል።
አምባሳደር ዓለምጸሀይ ኢትዮጵያ እና ኡጋንዳ ጠንካራ የሁለትዮሽ ግንኙነት እንዳላቸው ነገርግን ከግብይት ካላቸው አቅም እና ጆግራፊካዊ ቀረቤታ አንጻር የንግድ እና የኢንቨስትመንት ትስስሩ የሚጠበቀው ያህል አለመሆኑን ጠቅሰው፥ ለንግድ ትስስሩ መጠናከር የነሱ ተሳትፎ ወሳኝነት ያለው መሆኑን አስረድተዋል።
በመጨረሻም የንግድና ኢንቨስትመንት ስራዎችን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያግዝ በቀጣይ ወራት በኡጋንዳ የንግድ ማህበረሰቡን ያቀፈ የቢዝነስ ኮንፍረንስ ለማዘጋጀት እና ወደ ኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ጉብኝት ለማድርግ ስምምነት ላይ መደረሱን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!




0
People Reached
0
Engagements
Boost Post
Like
Comment
Share