Fana: At a Speed of Life!

ኢኮኖሚው የሚደርስበትን ጫና ለመቋቋም የአዳዲስ ስትራቴጂዎች ትግበራ ወሳኝ እንደሆነ ተጠቆመ

አዲስ አበባ፣ህዳር 7 ፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጦርነት ወቅት ምጣኔ ሃብቱ የሚደርስበትን ጫና ለመቋቋም እና የከፉ ችግሮችን ለመመከት የአዳዲስ ስትራቴጂዎች ትግበራ ወሳኝ እንደሆነ የዘርፉ ባለሙያዎች ተናገሩ፡፡
በሲቪል ሰርቪስ ዪኒቨርሲቲ የልማት ምጣኔ ሃብት ትምህርት ክፍል ተባባሪ ፕሬፌሰር እና ተመራማሪ ካሳ ተሻገር፥ በጦርነት ወቅት የሚያጋጥሙ ፈተናዎችን ታሳቢ ያደረጉ ስራዎች ትኩረት ሊሰጣቸው ይገባል ይላሉ፡፡
በተለይም ከጦርነት ቀጠና ዉጭ ያሉ አካባቢዎች የበለጠ ምርታማ ይሆኑ ዘንድ መንግስት ትኩረት ማድረግ ይገበዋል የሚሉት ተባባሪ ፕርፌሰር ካሳ ተሻገር፣ ሀገርን ከከፋ ችግር ለመታደግ የሚያስችሉ እና በርካታ አካላትን ያሳተፈ አስቸኳይ የመፍትሄ ስትራቴጂን ስራ ላይ ማዋል እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡
የፋና ብሮድካስቲንግ ባልደረባ ያነጋገራቸው ሌላኛው አስተያየት ሰጪ በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የምጣኔ ሀብት መምህርና ተመራማሪ አቶ እንዳልካቸዉ ሃብታሙ በበኩላቸው ፣ በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ወቅት ሃገር ያጋጠማትን የምጣኔ ሃብት ችግር ለመቋቋም ከተወሰዱ እርምጃዎች ትምህርት መዉሰድ ይገባል ባይ ናቸዉ ፡፡
ጦርነቱ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲጠናቀቅ መስራት ሀገርን ከከፋ የምጣኔ ሃብት ችግር ይታደጋል ያሉት ምሁራኑ ፣ ምጣኔ ሃብቱ ላይ ተጨማሪ ጫና የሚፈጥሩ የሃብት ምዝበራን የመሰሉ የሌብነት ተግባርን መቆጣጠር፥ ብሎም ተገቢዉን እርምጃ መዉሰድ እንደሚገባ ነው የገለጹት፡፡
የግሉ ዘርፍም በጦረነት ወቅት ከፍ ያለ ሀገራዊ ሚና ይኖረዉ ዘንድ ድጋፍና ክትትል የማድረጉ ጉዳይ መዘንጋት እንደሌለበት ጠቁመዋል፡፡
ሀገርን ከምጣኔ ሃብት ቀውስ የመታደጉ ጉዳይ ለአንድ ወገን የሚተዉ ባለመሆኑ ዜጎች፣ የግሉ ዘርፍ፣ መንግስትና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ከመቸዉም ጊዜ በበለጠ በርትተዉ በትብብር ሊሰሩ ይገባል ብለዋል የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎቹ።
በአወል አበራ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
May be an image of money
0
People reached
20
Engagements
Distribution score
Boost post
18
2 Comments
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.