በመኖሪያ ቤቱ ውስጥ የነዋሪነት መታወቂያ ሲያዘጋጅ የነበረ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ዋለ
አዲስ አበባ ፣ ህዳር 7 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በመኖሪያ ቤቱ ውስጥ የነዋሪነት መታወቂያን ጨምሮ የተለያዩ ሀሰተኛ ሰነዶችን ሲያዘጋጅ የነበረ በቦሌ ክፍለ ከተማ የወረዳ 07 አስተዳደር ሰራተኛ በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራው እየተጣራ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡
የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የወንጀል እና ትራፊክ አደጋ ምርመራ ዲቪዚዮን ሃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ዘሪሁን ተፈራ እንደገለጡት ፥ አንድ ግለሰብ ሀሰተኛ የነዋሪነት መታወቂያ ይዞ ሲንቀሳቀስ በህዝብ ጥቆማ በፖሊስ አባላት ተደርሶበት በተደረገ ምርመራ ሀሰተኛ መታወቂያውን ያዘጋጀውን ግለሰብ ማወቅና በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል፡፡
ሀሰተኛ ሰነዶቹን የሚያዘጋጀው ተጠርጣሪ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 አስተዳደር ወሳኝ ኩነት ምዝገባ የስራ መደብ ላይ ይሰራ የነበረ እና በአሁኑ ወቅት በሌላ የስራ መደብ ላይ የሚገኝ መሆኑን ሃላፊው ገልጸዋል።
ሃሰተኛ ክብ ማህተም እና ቲተሮችን በማስቀረፅ በመኖሪያ ቤቱ ውስጥ ህገ-ወጥ ሰነዶችን ሲያዘጋጅ ቆይቷልም ነው ያሉት፡፡
የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ህዳር 04 ቀን 2014 ዓ/ም ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 የረር በር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኘው በተጠርጣሪው መኖሪያ ቤት ባደረገው ብርበራ የተለያዩ ሰነዶች አግኝቷል።
ከሰነዶቹም መካከል ንግድ ፈቃዶች፣ የትምህርት ማስረጃዎች ፣ መሸኛ ደብዳቤዎች፣ የጋብቻ ማስረጃዎች እና ሌሎች ልዩ ልዩ ሰነዶች መገኘታቸውን ዋና ኢንስፔክተር ዘሪሁን ተፈራ ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪም ማህተሞች እና ቲተሮች፣ ፍላሾች፣ ላፕቶፕ ኮምፒውተር እና ፎቶግራፍ የተለጠፈባቸውን ጨምሮ ለሀሰተኛ የነዋሪነት መታወቂያ መስሪያ የሚገለገልባቸው በርካታ ካርዶች እና ሰሰተኛ ሰነዶች ሊያዘጋጅባቸው የተሰጡ የበርካታ ግለሰቦች ፎቶ ግራፎች በብርበራ መያዛቸውን ነው ሃላፊው ያስታወቁት ፡፡
በተጠርጣሪው ላይ ምርመራ እየተጣራ እንደሚገኝ ዋና ኢንስፔክተር ዘሪሁን አስረድተው፥ የአሸባሪው ህወሓት ቡድን ደጋፊዎች እና ሰርጎ ገቦች የሽብር ቡድኑን ተልዕኮ ለማስፈፀም ማንነታቸውን ቀይረው በከተማችን ለመንቀሳቀስ ሀሰተኛ ሰነዶችን ሊጠቀሙ እንደሚችሉ በመገንዘብ፥ ህብረተሰቡ ለፀጥታ አካላት እየሰጠ የሚገኘው ጥቆማ ለውጤታማ ስራዎች ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከተ በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ማለታቸውን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን




+2
0
People reached
0
Engagements
Boost post
Like
Comment
Share