Fana: At a Speed of Life!

የውጪ ሃይሎች የኢትዮጵያን እድገት በተለያዩ ጫናዎች ማዳከም ይሻሉ -የዌክአፕ አፍሪካ ሾው አዘጋጅ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በማልማት ለማደግ የምታደርገውን ጥረት በጦርነት ለማሰናከልና ለማዳከም የሚሰሩ ሃይሎች እንዳሉ የዌክአፕ አፍሪካ ሾው አዘጋጅ ዶክተር ሙምቢ ሴራኪ ተናገረች።
ኢትዮጵያ ላይ የተከፈተው ሁሉን አቀፍ ጫና ከጦርነቱም ቀድሞ ሲሰራበት መቆየቱን በመጥቀስ፥ በተለይም የህዳሴ ግድብን ለማሰናከል የተለያዩ ጫናዎች ሲደረጉ መቆየታቸውን አስታውሳለች።
“ግብፅ ከፈለገች ግድቡን ታፈነዳዋለች” መባሉንም በአብነት አንስታለች።
በኢትዮጵያ ላይ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎችና የእርዳታ ድርጅቶች የተቀናጀ ዘመቻ ስለመክፈታቸው አስረጂ የሚሆነው አንድ አይነት ቋንቋ መናገራቸው መሆኑን ትጠቅሳለች።
“ኢትዮጵያውያን ይህንን ለመመከት በውስጥም በውጪም አይበገሬነታቸውን ማሳየታቸው መልካም ነው” ብላለች።
ኢትዮጵያ ግድቡን በራሷ አቅም ለመስራት መወሰኗ ዓለም አቀፍ ጫናውን ለመቋቋም እንዳገዛት በመግለጽም፥ በዲፕሎማሲው አጋር የሆኗት ሩሲያና ቻይናም በኢትዮጵያ ጉዳይ የዓለም አቀፍ ጣልቃ ገብነትን አቅም ለመቀነስ እየረዳ መሆኑን ተናግራለች።
ኢትዮጵያን ለማዳከም በግልፅም በስውርም አሸባሪውን ህወሓት የሚደግፉ እንዳሉ የምትጠቅሰው አዘጋጇ፥ “በጦርነቱ የውጭ ቅጥረኞች መታየታቸው ለዚህ ተግባር አስረጂ ነው” ስትል ትገልጻለች።
“ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ግንባር ቀደም አገር እና የእድገት ምሰሶም በመሆኗ ልትደገፍ እና ልትጠበቅ ይገባል” ያለችው ዶክተር ሙምቢ፥ ከታሰበላት ወጥመድ ለመውጣት የህዝብ አንድነቷን ማጠናከር እንዳለባት ማስገንዘቧን ኢዜአ ዘግቧል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.