መገናኛ ብዙሃን የአገር ህልውና እና ብሔራዊ ጥቅም መከበር ቀዳሚ ስራቸው ሊሆን ይገባል
አዲስ አበባ ፣ ህዳር 9 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን የአገር ህልውና እና ብሔራዊ ጥቅም መከበር ቀዳሚ ስራቸው ሊሆን እንደሚገባ ኢዜአ ያነጋገራቸው የግል መገናኛ ብዙሃን ተቋማት ገለጹ፡፡
አንዳንድ የምዕራባውያን መገናኛ ብዙሃንና የዓለም አቀፍ ተቋማት በኢትዮጵያ ላይ የተቀናጀ ዘመቻ እያደረጉ መሆኑ ይታወቃል፡፡
በተለይም ስመ ጥር የሆኑ የምዕራባውያን ሚዲያዎች ሆነ ብለው መረጃን በማዛባት ኢትዮጵያን ለማፍረስ እየሰሩ ነው፡፡
የኢሳት ቴሌቪዥን የዜና ክፍል ኃላፊ አቶ ጌራ ጌታቸው እንደሚሉት፥ ኢሳት አሸባሪው ህወሓት አሁን እያደረሰ ያለውን ጥፋት መነሻ በማድረግ ብቻ ሳይሆን ቀደም ብሎ ቡድኑ ለኢትዮጵያ እንደማያስፈልግ ሲታገል እንደነበር አስታውሰዋል።
አሁን ላይ ጣቢያው የአገርን ህልውና ማስጠበቅ የሚያስችሉ የዜና እና ወቅታዊ ዝግጅቶችን ቀርፆ እየሰራ መሆኑንም ነው የተናገሩት።
ኢትዮጵያ አሁን ካለችበት ተጨባጭ ሁኔታ አንጻር እንደ ኢሳት ሁሉ ሌሎች የመገናኛ ብዙሃን ሙሉ ትኩረታቸውን የአገር ህልውና መጠበቅ ላይ ማድረግ እንዳለባቸው ገልጸዋል፡፡
በተመሳሳይ ለውጡን ተከትሎ ራሱን በአዲስ ስያሜ በማደራጀት የሚዲያ ዘርፉን የተቀላቀለው አዋሽ 90 ነጥብ 7 ኤፍ ኤም ሬዲዮ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅምና ህልውና መከበር ትኩረት አድርጎ ከሚሰሩ የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት መካከል ተጠቃሽ ነው፡፡
የአዋሽ ኤፍ ኤም ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ መሀመድ ሲራ፤ ሰርቶ መኖር የሚቻለው አገር ስትኖር ብቻ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ከ85 በመቶ በላይ የሚሆኑት የጣቢያው ዝግጅቶች አገራዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መሆናቸውንም ጠቁመዋል፡፡
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር መሀመድ እድሪስ በበኩላቸው፥ በኢትዮጵያ ፈቃድ ወስደው የሚሰሩ የግልም ሆኑ የህዝብ መገናኛ ብዙሃን የኢትዮጵያ ሀብት መሆናቸውን መገንዘብ እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡
በመሆኑም እነዚህ መገናኛ ብዙሃን አገርና ህዝብ አደጋ ላይ በሚወድቅበት ወቅት ዜጎች በጋራ በመቆም አደጋውን እንዲመክቱ ህዝብን ማንቃት ይጠበቅባቸዋል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ህብረተሰቡ ትክክለኛ መረጃን መሰረት ባደረገ መልኩ አገርን ለማዳን ለሚደረጉ ጥሪዎች ምላሽ እንዲሰጥ ሚናቸውን መወጣት እንዳለባቸው አንስተው ፥በተለይ አሸባሪው ህወሓት በሰላማዊ ዜጎች ላይ የሚፈፅመውን ግፍና መከራ ለአገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ በማጋለጥ ሚናቸውን መወጣት አለባቸው ብለዋል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!



0
People reached
68
Engagements
Boost post
66
2 Shares
Like
Comment
Share