አቶ ደመቀ መኮንን ከአሜሪካ የምሥራቅ አፍሪካ ልዩ ልዑክ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ ፣ ህዳር 9 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከአሜሪካ የምሥራቅ አፍሪካ ልዩ ልዑክ ጄፈሪ ፊልትማን ጋር ተወያዩ።
በውይይታቸው ወቅት ከአሸባሪው ህወሓት ጋር የሚደረገው ጦርነት ስለሚቆምበት መንገድ የአሜሪካ ሐሳብ ምን እንደሆነ በልዩ ልዑኩ በኩል የተነሣ ሲሆን፥ አቶ ደመቀም የኢትዮጵያን አቋም አስረድተዋል።
በኮምቦልቻና በላሊበላ ለሰብአዊ እርዳታ የሚውሉ በረራዎች መፈቀዳቸውን አቶ ደመቀ በዚህ ወቅት ገልጸዋል።
ወደ ትግራይም 369 እርዳታ የጫኑ መኪናዎች እንዲገቡ መፈቀዱን ጠቅሰው፥ በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የሚገኙ የአሜሪካ ዜጎችን ሁኔታ በተመለከተም ውይይት አድርገዋል።
አሸባሪው ሕወሓት አሁንም ቢሆን በአፋርና በአማራ ክልሎች ጥቃት እየፈጸመና ከፍተኛ ሰብአዊና ኢኮኖሚያዊ ውድመት እንዲሁም ስነልቦናዊ ጉዳት እያደረሰ መሆኑንም አስረድተዋል።
አያይዘውም ከሁለቱ ክልሎች ለቆ እንዲወጣ ግፊት ሊደረግበት እንደሚገባ ማሳሰባቸውን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት መረጃ ያመላክታል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

0
People reached
441
Engagements
–
Distribution score
Boost post
399
24 Comments
18 Shares
Like
Comment
Share