Fana: At a Speed of Life!

የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ  229 ተማሪዎችን አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ 229 ተማሪዎችን  በሚድዋይፈሪ ነርሲንግ ፣ፐብሊክ ሄልዝ እና ሜዲካል ላቦራቶሪ ያሰለጠናቸውን የመጀመሪያና ሁለተኛ ዲግሪ በዛሬው እለት አስመርቋል።

ዩኒቨርሲቲው በመጀመሪያ ዲግሪ ስድስት የትምህርት ክፍሎች እና በሁለተኛ ዲግሪ አራት የትምህርት ክፍሎች ያሉት ሲሆን፥ በልዩ ልዩ የጤና ፕሮግራሞች ተማሪዎችን ያሰለጥናል።

በምርቃት ስነ ስርአቱ ላይ የተገኙት የጤና ሚኒስትር ዲኤታ ሳህረላ አብዱላሂ ፥ ምርቃቱ የህዝብ ጤናን ሃላፊነት ለመውሰድ የምትዘጋጁበት ቀን ነው ሲሉ ለተመራቂዎች መልእክት አስተላልፈዋል።

ህክምና የተከበረ ሙያ ነው፤ እንደተከበረ ለማቆየትም የሙያውን ስነ ምግባር ተላብሶ በክብርና ርህራሄ ህብረተሰቡን ማገልገል ይጠበቅባችኋልም ነው ያሉት ።

በምርቃር ስነ ስርአቱ ላይ ፥ የተለያዩ የመንግስት ሃላፊዎች፡ አባገዳዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ በጤናው ዘርፍ ተማሪዎችን መቀበል የጀመረው ከ1999 ጀምሮ ነው።

በመአዛ መላኩ

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.