Fana: At a Speed of Life!

የአሸባሪው ህወሓት አክቲቪስቶችና ደጋፊ የምዕራባዊያን ሚዲያዎች “ሁመራ ማሳከር” የሚል ሀሰተኛ ዘመቻ ለመጀመር ዝግጅት ማጠናቀቃቸው ተደርሶበታል

 

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 13 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሸባሪው ህወሓት አክቲቪስቶችና ደጋፊ የምዕራባዊያን ሚዲያዎች “ሁመራ ማሳከር” የሚል ሀሰተኛ ዘመቻ ከዚህ በፊት እንዳደረጉት ሁሉ ለመጀመር ዝግጅት ማጠናቀቃቸው ተደርሶበታል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ትናንት ኬንያዊው የደህንነት ጉዳዮች ተንታኝ የኢትዮጵያን እውነት በማዛባትና ሀሰተኛ መረጃ በማሰራጨት የሚታወቁት ሚዲያዎች በሱዳን ገዳሪፍ ግዛት መሰባሰባቸውን አጋልጦ ነበር።
የኢፕድ ምንጮች የአሸባሪው የጥቅም ተጋሪዎችና ተከፋይ አክቲቪስቶች በሁመራ የጅምላ ጭፍጨፋ ተፈጽሟል በሚል ዘመቻ ለመጀመር ዝግጅት ማጠናቀቃቸውን ገልጸዋል።

ይህ የአሸባሪው የዲጂታል ክንፍ ከዚህ በፊትም ተመሳሳይ የሀሰት ዘመቻ በመክፈት መንግስትን ለመወንጀል ዝግጅት ማጠናቀቁን መረጃው የደረሰው መንግሥት አስቀድሞ በአስቸኳይ ጊዜ መረጃ ማጣሪያ ገጽ ላይ ማስጠንቀቂያ አውጥቶ እንደነበር የሚታወስ ነው።

አስቀድሞ የተጋለጠው የጁንታው አክቲቪስትና እነሲኤንኤን ያሰቡትን ሳያሳኩ ቀርተዋል።

በወቅቱ በመስከረም ወር ላይ የCNN ዘጋቢዋ ኒማ ተመሳሳይ የሀሰት ዘገባ መስራቷና በምንጭነትም የአሸባሪው ህወሓት አመራር የሆኑትን እና ገሬ የተባለውን ሰው እንዲሁም የቡድኑን አባላትና በማይካድራ ጭፍጨፋ የሚፈለጉ ነፍሰ ገዳዮችን በምንጭነት መጠቀሟ በስፋት በማህበራዊ ሚዲያ መጋለጡ አይዘነጋም።

በወቅቱ በሱዳን ጉብኝት ሲያደርጉ የነበሩት የዩ ኤስ አይዲ ሃላፊ ሳማንታ ፓወር አስቀድመው በትዊተር ገጻቸው ላይ ስለጉዳዩ መጻፍ ጀምረውም ነበር።

አሸባሪው ህወሓት በእርዳታ ዱቄት ሳይቀር እያስፈራራ እና ቤት ለቤት እያፈሰ በህዝብ ማዕበል ወደ ውጊያ የላከውን ወጣት ካስጨረሱ በኋላ አስከሬናቸውን ወደ ወንዝ በመጨመር “ሁመራ ማሳክር” በማለት ሀሰተኛ መረጃ ለማሰራጨት ዛሬም ዝግጅታቸውን ማጠናቀቃቸውን ምንጪቻችን ነግረውናል።
አሁን ሁመራ ማሣከር በሚል ለመልቀቅ እየተዘጋጁበት ላለው ሴራም ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን በተለይም ሱዳን ተሰባስበው ይገኛሉ።

ምዕራባዊያን መገናኛ ብዙኃን የአሸባሪው ህወሓትን ሀሰተኛ መረጃ ለመዘገብ በሱዳን እየተሰባሰቡ ነው ሲል ኬንያዊው የወንጀል ምርመራና የደህነንት ጉዳዮች ተንታኝ ኮሊንስ ዋንደሪ በይዊተር ገጹ ላይ ማስታወቁም ይታወሳል።

የአሸባሪው ህወሓት ደጋፊ ሆነው ኢትዮጵያን በተመለከተ ሀሰተኛ መረጃ እያሰራጩ የሚገኙት ቢቢሲ፣ ሲኤንኤን፣ ሮይተርስ፣ አሶሼትድ ፕሬስ፣ አልጀዚራ፣ ቴሌግራፍ፣ ፍራንስ 24 እና ሌሎች ምእራባዊያን መገናኛ ብዙኃን አሸባሪው ህወሓትን በመደገፍ ሀሰተኛ መረጃዎችን ለማሰራጨት በሱዳን ገዳሪፍ ግዛት እየተሰባሰቡ መሆኑን አጋልጧል።

መገናኛ ብዙኃኑ በሱዳን ገዳሪፍ ግዛት ዋድ ሙዛሚል በተባለችው ከተማ መሰባሰባቸውን ያጋለጠው ኬኒያዊው ተንታኝ በሱዳን መንግስት ደጋፍ እየተደረገላቸው መሆኑንም ገልጿል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.