ቡድኑ በሚነዛው የሀሰት ፕሮፖጋንዳ አካባቢን መልቀቅ አይገባም – የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር
አዲስ አበባ፣ ህዳር 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪውን የህወሓት ቡድን ለመደምሰስ በግንባር ተፋልሞ ማሸነፍ እንጂ ቡድኑ በሚነዛው የሀሰት ፕሮፖጋንዳ አካባቢን መልቀቅ አይገባም ሲል የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር አስታውቋል።
የከተማ አስተዳደሩ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ደስታ አንዳርጌ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳሉት፥ የደብረ ብርሃን ከተማ እና አካባቢዋ ነዋሪዎች የጥፋት ቡድኑን በመፋለም የማንበርከክ ታሪካዊ ሃላፊነት አለባቸው።
የሸዋ ህዝብ የጀግንነት ታሪክ ያለው ነው ያሉት ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው፥ የሽብር ቡድኑን ለመደምሰስ ሁሉም የከተማው ነዋሪዎች በእልህ እና በቁጭት ከመከላከያ ጎን በመሰለፍ እንዲመክቱ ጥሪ አቅርበዋል።
በአንድ ልብ ጠላትን ከተዋጋን የማናስመዘግበው ድል የለም ያሉት አቶ ደስታ፥ ሰርጎ ገቦችን በመቆጣጠር እና ዘመቻውን በመቀላቀል አገር የማዳን ሃላፊነትን መወጣት እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል።
በታለ ማሞ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!