Fana: At a Speed of Life!

በክፍለ ከተማው ልዩ ልዩ የጦር መሳሪያና ወታደራዊ አልባሳት ተያዙ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በህብረተሰቡ ጥቆማ በአንድ መኖሪያ ቤት በተደረገ ብርበራ በርካታ የጦር መሳሪያና ልዩ ልዩ ወታደራዊ አልባሳት መያዛቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡
በዛሬው ዕለት ፖሊስ ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ ፥ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 አያት ዞን ሁለት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በአንድ መኖሪያ ቤት ባደረገው ፍተሻና ብርበራ 5 የእጅ ቦንብ፣ 1 ክላሽንኮቭ ጠብ መንጃ ከመሰል 190 ጥይቶች እና 5 ካርታ ጋር፣ 1 ሳንጃ፣ የትጥቅ መያዣ ወታደራዊ ቀበቶ፣ የጥይት መከላከያ፣ የሱዳን፣ የኤርትራና የቀድሞው የሀገር መከላከያ ሰራዊት የደንብ አልባሳት እንዲሁም ልዩ ልዩ ሰነዶችና ማህተሞች ማግኘቱን ፖሊስ አስታውቋል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
+4
0
People reached
0
Engagements
Boost post
Like

 

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.