የኩዌት ህዝብና መንግስት ለተፈናቃዮች 7 ሚሊየን የሚገመት የምግብና አልባሳት ድጋፍ አደረገ
አዲስ አበባ ፣ ህዳር 17 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኩዌት ህዝብና መንግስት በደብረ ብርሃን ከተማ ለሚገኙ ተፈናቃዮች ከ7 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው የምግብና አልባሳት ድጋፍ አድርጓል።
የኩዌት ህዝብና መንግስት፤ በኩዌት ዳይሬክት ኤድ በኩል በደብረ ብርሃን ከተማ ለሚገኙ ተፈናቃዮች የምግብ አቅርቦትና የብርድ ልብስ ድጋፍ አድርጓል።
ኩዌት ዳይሬክት ኤድ በደብረ ብርሃን ከተማ በመገኘት ከ7 ሚሊዮን በላይ ወጭ የተደረገበትን ሩዝ፣ ዘይት እንዲሁም ብርድ ልብስ ለተፈናቃዮቹ አከፋፍሏል።
የኩዌት ዳይሬክት ኤድ ካንትሪ ዳይሬክተር ጣሃ መሀመድ፤ በኢትዮጵያ ሰብአዊ ድጋፍ ሲያደርጉ የመጀመሪያቸው እንዳልሆነ ጠቅሰዋል።
ከዚህ ቀደም በአፋር በጎርፍ አደጋ ለተጎዱ ሰዎች፣ በኮቪድ እና ሌሎች ምክንያቶች ችግር ላይ ለነበሩ ዜጎች ድጋፍ መደረጉን አስታውሰዋል።
”የአሁኑ ድጋፍም የትብብራችን አንዱ ማሳያ ነው ያሉት ዳይሬክተሩ ድጋፉን አጠናክረን እንቀጥላለን” ሲሉ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
በዛሬው እለትም በደብረ ብርሃን ከተማ በመገኘት ለተፈናቃዮች የምግብ አቅርቦትና የብርድ ልብስ ድጋፍ መደረጉን ገልጸዋል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!