Fana: At a Speed of Life!

አፍሪካ የሠላም እና የደኅንነት ተግዳሮቶቿን በራሷ መፍታት አለባት – ኃይለማሪያም ደሳለኝ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አፍሪካ ለሠላም እና ደኅንነት ተግዳሮቶች ከውጭ መፍትሄ ከመሻት አስቀድማ በራሷ ለመፍታት መሥራት እንዳለባት የኢፌዴሪ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ገለጹ፡፡ ትናንት የተጠናቀቀው የጣና ፎረም “የአኅጉሪቷ ሠላምና ደኅንነት…

የኅዳሴ ግድብ የአንድነታችን ማሰሪያ በመሆኑ ለፍጻሜ ለማብቃት በትብብር እንሠራለን – የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ የአንድነታችን ማሰሪያ በመሆኑ የፖለቲካ ልዩነት ሳይገድበን ለፍጻሜ ለማብቃት በትብብር እንሰራለን ሲሉ የተለያዩ የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ገለጹ፡፡ በታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ በመገኘትም የግንባታውን ሂደትና…

በሰሜን ኢትዮጵያ የሚካሄደውን የመከላከል ርምጃ በተመለከተ የተሰጠ መግለጫ

በአሁኑ ወቅት በሰሜን ኢትዮጵያ የተፈጠረው ግጭት፤ ሕወሐት ነሐሴ 18 ቀን 2014 ዓ.ም በሙሉ ዐቅሙ የከፈተውን ጥቃት ተከትሎ የመጣ መሆኑን ማስታወስ ተገቢ ነው። ይህም የኢትዮጵያ መንግሥት በሚያዝያ ወር ያወጀውን በሰብአዊነት ላይ የተመሠረተ የተኩስ አቁም የጣሰ ነው። የመንግሥት ጥረት ምንም ዋጋ…

በፓኪስታን የኢትዮጵያ ኤምባሲ በሲንድ ግዛት በጎርፍ ለተጎዱ ፓኪስታናውያን የሰብዓዊ ዕርዳታ አቀረበ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 7 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በፓኪስታን የኢትዮጵያ ኤምባሲ አምባሳደር ጀማል በከር ከ8 ሺህ ለሚበልጡ የሲንድ ግዛት የጎርፍ ተጎጂዎች ድጋፍ አቅርበዋል፡፡ ድጋፉም ምግብ፣ መድኃኒት፣ መጠለያ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶችን ያካተተ መሆኑን ከኤምባሲው ያገኘነው መረጃ…

10ኛው የጣና ፎረም ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 6 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ለቀናት በባህር ዳር ሲካሄድ የቆየው 10ኛው የጣና ፎረም ተጠናቀቀ። ጉባዔው የተካሄደው "የደኅንነት ሥጋቶችን መቆጣጠር ፣ተጽዕኖን የመቋቋም አቅምን በአፍሪቃ ለመገንባት" በሚል መሪ ቃል ነው፡፡ ፎረሙ በርካታ ነጥቦች የተነሱበትና ውጤታማ…

በገንዘብ ሚኒስትሩ የተመራው ልዑክ ከ“አይ ኤም ኤፍ” ሥራ አስፈጻሚ ዳይሬክተሮች ጋር ተወያየ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 6 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)በገንዘብ ሚኒስትሩ አሕመድ ሺዴ የተመራው ልዑክ ከዓለምአቀፉ የገንዘብ ተቋም ሥራ አስፈጻሚ ዳይሬክተሮች ጋር ፍሬያማ ውይይት ማካሄዱ ተገለጸ፡፡ ልዑካን ቡድኑ ከዓለምአቀፉ የገንዘብ ተቋም ሥራ አስፈጻሚ ዳይሬክተሮች ጋር የመከረው በአሜሪካ እየተካሄደ…

በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ የምዕራባውያን አተያይ የተዛባ ነው – ፕሮፌሰር አን ፊትዝ ጄራልድ

አዲስ አበባ፣ጥቅምት 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ለተከሰተው ግጭት መራዘም የምዕራባውያን አተያይና ምላሽ ሚዛናዊ አለመሆን የበኩሉን አስተዋፅዖ ማበርከቱን ፕሮፌሰር አን ፊትዝ ጄራልድ ገለጹ፡፡ በካናዳ የዓለም አቀፍ ጉዳዮች ትምህርት ቤት ዳይሬክተር የሆኑት ፕሮፌሰር አን ፊትዝ ጄራልድ…

40 ኤፍ1 ቦምብ እና 15 ክላሽንኮቭ መሳሪያ ተያዘ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በምዕራብ ጎንደር ዞን ዞን መተማ ወረዳ በማጠቢያ ንዑስ ወረዳ ጉባይ ቀበሌ ለሽብር ተግባር ሊውል የነበረ 40 ኤፍ1 ቦምብ መያዙን ፖሊስ አስታውቋል፡፡ የመተማ ወረዳ ፖሊስ የታክቲክ ምርመራ ክፍል ኃላፊ ረዳት ኢንስፔክተር ቸኮል ወርቄ እንደገለጹት÷…

የታዳጊ ሀገራት ኢኮኖሚ በወቅታዊ ሁኔታ እጅጉን እየተፈተነ ነው – አይ ኤም ኤፍ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ታዳጊ ሀገራት እና አዳዲስ ገበያዎች በዶላር ዋጋ መወደድ፣ በከፍተኛ የብድር ወለድ ጫና እና በንግድ ሰበብ ከሀገራቱ ወደ ውጪ በሚንቀሳቀስ ሐብት ኢኮኖሚያቸው እጅጉን እየተፈተነ መሆኑን ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም አስታወቀ፡፡ በተለይም ከፍተኛ…

የኢትዮጵያ አረንጓዴ ልማት ዲፕሎማሲ የወጣቶች ልዑክ ካርቱም ገባ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ወንድማማችነትን እና የአረንጓዴ ልማት ዲፕሎማሲን ዓላማ ለማስተዋወቅ የኢትዮጵያ የወጣቶች ልዑክ ካርቱም ገባ፡፡ ወደ ካርቱም ያመራው የኢትዮጵያ ወጣቶች ልኡካን ቡድን በዴሞክራሲ ሥርአት ግንባታ ማዕከል ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሙሳ አህመድ…