Fana: At a Speed of Life!

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ዘላቂ ሠላም ለማስፈን ያለመ ውይይት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ዘላቂ ሠላም ለማስፈን ያለመ ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡ መድረኩ በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሃሰን እና በከፍተኛ አመራሮች ልዑክ እየተመራ መሆኑ ተገልጿል፡፡ ባለፉት ዓመታት እንደ ሀገር ከፍተኛ…

ኮኬይን ሲያዘዋውር ተገኝቷል የተባለ የውጭ ዜጋን በማስመለጥ የተጠረጠሩ 2 የፌዴራል ፖሊስ ዋና ኢንስፔክተሮች ዋስትና ታገደ

አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ 27 ነጥብ 5 ኪሎ ግራም ኮኬን ዕፅ የያዘ የውጭ ዜጋን አስመልጠዋል የተባሉ ሁለት የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ዋና ኢንስፔክተሮች የተፈቀደላቸው የዋስትና መብት ታገደ። ተጠርጣሪዎቹ ዋና ኢኒስፔክተር አዲሱ ባሌማ እና ዋና…

ምዕራባውያን ለዩክሬን መሣሪያ ማቀበላቸውን ከቀጠሉ ዓለም አቀፍ ውድመት ሊከሰት እንደሚችል ሩሲያ አስጠነቀቀች

አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ምዕራባውያኑ ለዩክሬን መሣሪያ ማቀበላቸውን የሚገፉበት ከሆነ ዓለም አቀፍ ውድመት ሊከሰት እንደሚችል የሩሲያ ፓርላማ አፈ ጉባኤ ቪያቼስላቭ ቮሎዲን አስጠነቀቁ። አፈ ጉባኤው ምዕራባውያን ሀገራት ለዩክሬን በሚያደርጉት ድጋፍ የሩሲያ የሩሲያ ሉዓላዊነት…

በኦሮሚያ ክልል የ2015 የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ሥራ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል የ2015 የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በዛሬው ዕለት በአዳማ ወረዳ ተካሂዷል፡፡ በመርሐ ግብሩ የብልጽግና ፓርቲ ኦሮሚያ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ የሥራ…

መስዋዕትነት ለከፈሉ ዓርበኞች ልጆች የሕፃናት መርጃ ማዕከል የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ

አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኅልውና ዘመቻው ለሀገር መስዋዕትነት ለከፈሉ ጀግኖች ዓርበኞች ልጆች ማሳደጊያ የሚውል የሕፃናት መርጃ ማዕከል በጎንደር ከተማ ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ፡፡ የመርጃ ማዕከሉ የመሰረት ድጋይ በጎንደር ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ዘውዱ ማለደ…

የሶማሌ ክልል የ6 ወራት የሥራ አፈፃፀም እየገመገመ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል የ2015 የስድስት ወራት የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች፣ የዞንና የከተማ አስተዳደሮች የሥራ አፈፃፀም ግምገማ እየተካሔደ ነው፡፡ በግምገማው ላይ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ፣ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ኢብራሂም ኡስማን፣…

ጥምቀትን በአብሮነት በማክበራችን ተደስተናል – የአክሱም ከተማ ነዋሪዎች

አዲስ አበባ፣ ጥር 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ለዓመታት ርቆን የቆየው ሰላም ተመልሶ ጥምቀትን በአብሮነት በማክበራችን ተደስተናል ሲሉ የአክሱም ከተማና አካባቢው ነዋሪዎች ገለጹ። የጥምቀት በዓል በታሪካዊቷ አክሱም ከተማና ሌሎች የትግራይ ክልል አካባቢዎች ተከብሯል። አስተያየት…

በሦስት የእሳት አደጋዎች 6 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት ወደመ

አዲስ አበባ፣ ጥር 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ እና አካባቢዋ በተከሰቱ ሦስት የእሳት አደጋዎች 6 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት መውደሙን የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ በሦስቱም አደጋዎች በሰው ላይ ጉዳት አለመድረሱ እና ከ900…

በጃንሜዳ በጥምቀት በዓል ላይ ስርቆት ፈጽመዋል የተባሉ 13 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ ጥር 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ጃንሜዳ የከተራ እና ጥምቀት በዓል ላይ የስርቆት ወንጀል ፈጽመዋል የተባሉ 13 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋቸውን ፖሊስ አስታወቀ፡፡ የተሰረቁ 20 ሞባይል ስልኮችም በኤግዚቢትነት መያዛቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ መረጃ…

አዋሽ ባንክ እና የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በጋራ ለመስራት ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ጥር 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አዋሽ ባንክ እና የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢኒስቲትዩት በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡ ስምምነቱን የአዋሽ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፀሐይ ሽፈራው እንዲሁም የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢኒስቲትዩት ዋና…