Fana: At a Speed of Life!

በክልሉ በአረንጓዴ ዐሻራ ከ300 ሚሊየን በላይ ችግኞችን ለመትከል ዝግጅት እየተደረገ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በዘንድሮው ክረምት የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ከ300 ሚሊየን በላይ ችግኞችን መትከል የሚያስችል ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል፡፡ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት እንዳስታወቀው ÷ አረንጓዴ ዐሻራ በሁሉም መስክ ምርታማነትን…

ከደሴ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ በነበረ ተሽከርካሪ ላይ በደረሰ አደጋ የ28 ሰዎች ሕይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ከደሴ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ በነበረ ተሽከርካሪ ላይ በደረሰ አደጋ የ28 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ፖሊስ አስታውቋል። አደጋው የደረሰው በዛሬው ዕለት ከደሴ እና ኮምቦልቻ ከተሞች መካከል በሚገኘው የሐረጎ መንገድ ላይ መሆኑም ነው የተገለጸው፡፡…

‎ሰራዊቱ የማይወዛወዝ ምሰሶ በመሆን ሀገር የማሻገር ተልዕኮውን እየተወጣ ነው – ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) መከላከያ ሰራዊቱ ‎የማይወዛወዝ ምሰሶ በመሆን ሀገር የማሻገር ተልዕኮውን እየተወጣ ነው አሉ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ፡፡ ‎ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በማዕከላዊ ዕዝ መኮንኖች የግዳጅ አፈፃፀምና ቀጣይ አቅጣጫዎች…

የኢትዮጵያ ተስፋ የሚለመልመው በሰለጠነ የፖለቲካ አውድ ነው – ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ የኢትዮጵያ ተስፋ የሚለመልመው በሰለጠነ የፖለቲካ አውድ ነው አሉ፡፡ የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ም/ቤት በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ባለድርሻ አካላት የእውቅናና የምስጋና መርሐ ግብር አካሂዷል።…

71ኛው የቱለማ ገዳ የስልጣን ሽግግር…

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ከአምስቱ የኦሮሞ ገዳዎች አንዱ የሆነው የቱለማ ገዳ የ71ኛው ዙር የስልጣን ርክክብ ማጠቃለያ በነገው ዕለት በዳካ ኮራ አርዳ ጂላ ይካሄዳል። የኦሮሞ ገዳ ሥርዓት ለብዙ ዘመናት የዘለቀና ዓለም ያደነቀው የማይዳሰስ ቅርስ ሲሆን፥ የማኅበረሰቡን ባህል፣…

ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን የቀድሞ የቦርድ ሰብሳቢ ሙአዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ሽኝት ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን የሥራ አመራር ቦርድ የቀድሞ ሰብሳቢ ሙአዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ሽኝት ተደረገላቸው። በሽኝት መርሐ ግብሩ ላይ የፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን የቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ኃላፊነቱን የተረከቡት የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት…

አቶ ደስታ ሌዳሞ በ2 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ወጪ የተሰሩ ፕሮጀክቶችን መርቀው ስራ አስጀመሩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ በ2 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ወጪ የተሰሩ ፕሮጀክቶችን መርቀው ስራ አስጀምረዋል፡፡ ለአገልግሎት ክፍት ከተደረጉት ፕሮጀክቶች በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የሚገኙ ዘመናዊ ማዕከላዊ የቀዶ…

በሀገራዊ ጉባኤው ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ ጽኑ መሰረት እንጥላለን – ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ (ፕ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ሀገራዊ የምክክር ጉባኤው በመሰረታዊ አጀንዳዎች ላይ በሰለጠነ መንገድ በመነጋገር ለዘላቂ ሰላም ጽኑ መሰረት የሚጣልበት ነው አሉ ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ (ፕ/ር)። የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሀገራዊ የምክክር ጉባኤው ከሐምሌ 8/2018 ዓ.ም ጀምሮ…

ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ በመጪው ሐምሌ 8 ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ከሐምሌ 8/2018 ዓ.ም ጀምሮ ይካሄዳል አለ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን፡፡ ኮሚሽኑ ሀገራዊ የምክክር ጉባኤውንና ተያያዥ ጉዳዮችን በተመለከተ በዛሬው ዕለት መግለጫ ሰጥቷል፡፡ በ12 ክልሎችና በሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች…

አየር መንገዱ ከነገ ጀምሮ ወደ ደብረማርቆስ ከተማ በረራ ሊያደርግ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከነገ ሰኔ 6 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ደብረማርቆስ ከተማ የቅድመ ምረቃ በረራዎችን እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡ መንገደኞች የበረራ ቲኬቶችን በሁሉም የቲኬት መሸጫ ቢሮዎች ማግኘት እንደሚችሉ የአየር መንገዱ መረጃ…