Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና ደቡብ አፍሪካ በወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦችን አሳልፎ ለመስጠት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያና ደቡብ አፍሪካ በወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦችን አሳልፎ ለመስጠት የሚያስችል ስምምነት ተፈራርመዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ የደቡብ አፍሪካ የዓለም አቀፍ ግንኙነቶችና ትብብር ሚኒስትር ዶክተር ናሌዲ…

የአዲስ አበባ ፍትህ ቢሮ ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመከላከል ከ22 ድርጅቶች ጋር ተፈራረመ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ፍትህ ቢሮ መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን በጋራ ለመከላከል የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ። ስምምነቱን የአዲስ አበባ ፍትህ ቢሮ ኃላፊ ተክሌ በዛብህ ከ22 ተቋማት ኃላፊዎች ጋር…

የዓለም ኢኮኖሚ መስከን እያሳየ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም ኢኮኖሚ መስከን እያሳየ መሆኑን ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይ ኤም ኤፍ) ገለጸ፡፡ ዓለማቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ) አሻሽሎ ባወጣው ሪፖርቱ የዓለም ኢኮኖሚ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ ባጋጠሙ የተለያዩ እክሎች ምክንያት ቀውስ…

በከፍተኛ ሙቀት ምክንያት በተከሰተ ሰደድ እሳት ከ40 በላይ ሰዎች ለህልፈት ተዳረጉ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በከፍተኛ ሙቀት ምክንያት በተከሰተ ሰደድ እሳት ከ40 በላይ ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸው ተሰማ። በአልጄሪያ፣ ጣሊያን እና ግሪክ የሰደድ እሳቱ ወደመንደሮችና መዝናኛ ቦታዎች ላይ በመስፋፋቱ የዜጎች ህይወት ማለፉ የተገለጸው፡፡ ከዚህ ባለፈም…

የጠ/ሚኒስትሩ የሮም ቆይታ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ መድረክ ስኬታማ የዲፕሎማሲ ስራ ያከናወነችበት ነው – ቢልለኔ ሥዩም

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጠቅላይ ሚኒስትሩ የሮም ቆይታ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ መድረክ ልምድና ተሞክሮዋን ያጋራችበትና ስኬታማ የዲፕሎማሲ ስራ ያከናወነችበት መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ሃላፊ ቢልለኔ ስዩም ተናገሩ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ…

የሸገር ዳቦ ምርትን መልሶ ለመጀመር ሒደት ላይ መሆኑን የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሸገር ዳቦ ምርትን መልሶ ለመጀመር ሒደት ላይ መሆኑን የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ አስታውቋል፡፡ በቀን 1 ሚሊየን ዳቦ የሚያመርተው ድርጅቱ ምርቱ በመዲናዋ መሰራጨቱ ከቆመ ሁለት ወራት ተቆጥረዋል። የሸገር ዳቦ ምርት የቆመበት ምክንያት…

በደብረ ብርሃን ፀጥታ አካላት ላይ ተኩስ ከፍተው ነበር በተባሉ 21 ተጠርጣሪዎች ላይ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ተፈቀደ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ፍርድ ቤቱ በደብረ ብርሃን ፀጥታ አካላት ላይ ተኩስ ከፍተው ነበር ተብለው በሽብር ወንጀል ከተጠረጠሩ ከ25 ግለሰቦች መካከል 21 ተጠርጣሪዎች ላይ ተጨማሪ ምርመራ እንዲደረግ የ14 ቀን ጊዜ ፈቀደ። በመዝገቡ የተካተቱ ሌሎች አራት ተጠርጣሪዎችን…

የትግራይ ክልል ካቢኔ ጊዜያዊ አስተዳደር የ2016 ዓ.ም ከ17 ቢሊየን ብር በላይ በጀት አፀደቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 18 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የትግራይ ክልል ካቢኔ ጊዜያዊ አስተዳደር የ2016 ዓ.ም በጀት ዓመት 17 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር በማድረግ አፀደቀ። ካቢኔው ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ ÷ የቀረበለትን የ2016 ዓ.ም ረቂቅ በጀት በዝርዝር እንደተወያየ ተገልጿል። በዚህ መሰረት…

በኮንፌዴሬሽን ካፕ ኢትዮጵያን የሚወክለው ባህር ዳር ከተማ ተጋጣሚውን አውቋል

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 18 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በካፍ ኮንፌዴሬሽን ካፕ ኢትዮጵያን የሚወክለው ባህር ዳር ከተማ ተጋጣሚውን አውቋል። ክለቡ በመጀመሪያው ዙር የኮንፌዴሬሽን ማማጣሪያ ከታንዛኒያውአዛም ጋር ጨዋታውን የሚያደረግ ይሆናል። ይህን ጨዋታ ካሸነፈ ደግሞ በሁለተኛው ዙር ማጣሪያ ደግሞ…

ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲን የ12ኛ ክፍል ፈተና ቅድመ ዝግጅት ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 18፣ 2015(ኤፍ ቢ ሲ) የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ተገኝተው የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና የቅድመ ዝግጅትና የተማሪዎች አቀባበል ሁኔታን ተመልክተዋል። ሚኒስትሩ ከሶማሌ ብሔራዊ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ጋር በመሆን ነው…